ማብቂያ ያጣዉ የስደተኞች እልቂት በሜዲተራንያን | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 31.05.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

ማብቂያ ያጣዉ የስደተኞች እልቂት በሜዲተራንያን

የስደተኞች ስቃይ ዋይታና ሞት ዛሬም በአዉሮጳ ምሥራቃዊና ደቡባዊ ድንበሮች እየተሰማ ነዉ። ባለፈዉ ሳምንት ብቻ ከሊቢያ የባህር ጠረፍ ሜዲተራንያንን ባህር አቋርጠዉ ወደ አዉሮጳ ለመሻገር ከሞከሩት በሺ ከሚቆጠሩት ስደተኞች ዉስጥ ከ 900 በላይ የሆኑት የዉኃ እራት ሆነዉ መቅረታቸዉ በአደባባይ ተገልጾአል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 07:12
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
07:12 ደቂቃ

የስደተኞች እልቂት በሜዲተራንያን


እነዚህ በብዛት ከአፍሪቃ ሃገራት እንደመጡ የሚነገርላቸዉ ስደተኞች ሩቅ አስበዉ በአጭር የተቀጩት ወጣቶችና ጨቅላ ሕጻናት ጭምር በአሳዛኝ ሁኔታ ሕይወታቸዉ ያለፈዉ ይቀዝፉበት የነበረዉ ጀልባ ተገልብጦ ፤ ተሰብሮ አልያም ተበላሽቶ መሆኑ ከመገለፁ ዉጭ አስክሬን እንኳ የተገኘዉ የጥቂቶች ብቻ መሆኑ ነዉ የተነገረዉ። ይህ የሆነዉ የዛሬ ሦስት ዓመት በዚያዉ በሜዲተራንያን ባሕር ላይ በኢጣልያ የላምፔዱዛ ደሴት አካባቢ ስደተኞችን የጫነች ጀልባ ተገልብጣ ከሦስት መቶ በላይ የሚሆኑ ስደተኞች ከሞቱ በኋላ የአውሮጳ ህብረት ተመሳሳይ አደጋ እንዳይፈጠር በርካታ ርምጃዎችን መውሰዱን እና የነፍስ አድን ግብረ ኃይልንም ማቋቋሙን በገለጸ ማግስት ነዉ። በዛሬው አውሮጳ እና ጀርመን ዝግጅት ማብቂያ ያጣውን የስደተኞች ስቃይና እልቂት ከአዉሮጳ የስደተኞች ፖሊስ ስምረትና ጉድለት ጋር እያነጻጸርን እናያለን።ገበያዉ ንጉሴ

አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic