ማሪየንቦርን ሄልምሽታት የቁጥጥር ኬላ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 11.11.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

ማሪየንቦርን ሄልምሽታት የቁጥጥር ኬላ

ለ40 አመታት ገደማ ጀርመን ምዕራቡን ከምሥራቅ እንዳይገናኝ በሚያግድ ግንብ ለሁለት ተከፍላ ቆይታለች። ግንቡን ለመገንባት እቅዱን ያመነጨው የወቅቱ የምሥራቅ ጀርመን መንግሥት ዓላማው ዜጎችን ከፋሽስታዊ አስተሳሰብ ለመጠበቅ ነበር።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 08:52

ከፈረሰ 30 ዓመት ያለፈው ግንብ አሻራ

 በእነዚያ 40 ገደማ አመታት ከ100,000 በላይ ሰዎች ከምሥራቅ ጀርመን ወደ ምዕራብ ጀርመን ለማምለጥ ሞክረው 5,000 ያክሉ ተሳክቶላቸዋል። በርካቶች በጥበቃ ማማዎች ላይ ባደፈጡ ወታደሮች በተተኮሱ ጥይቶች ተገድለዋል። ዛሬም ትክክለኛውን የሟቾች ቁጥር ለማወቅ ምርመራ እየተደረገ ቢሆንም አንዳንድ ዘገባዎች እንደሚሉት ከምሥራቁ ወደ ምዕራቡ ለመሻገር በተዘጋጁ መተላለፊያዎች እስከ1,000 የሚደርሱ ሰዎች ተገድለዋል። ማሪየንቦርን ግንቡ ግዘፍ ነስቶ ሁለቱን ጀርመኖች በከፈለባቸው አመታት ትልቁ እና ከፍ ያለ ሚና የነበረው መተላለፊያ ነው። ወደ ቦታው አቅንቶ የነበረው እሸቴ በቀለ ተጨማሪ ዘገባ አለው። ሙሉ ቅንብሩን ከድምፅ ዘገባው ያድምጡ፤

እሸቴ በቀሌ 

ተስፋለም ወልደየስ

Audios and videos on the topic