ማሊ-ጥቃት በቲምቡክቱ ከተማ ላይ | አፍሪቃ | DW | 02.07.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

ማሊ-ጥቃት በቲምቡክቱ ከተማ ላይ

በዓለም ቅርስነት ጥበቃ የሚደረግላት የማሊዋ የቲምቡክቱ ከተማ ላይ አንሣር-ዲን በተባለው ቡድን ጥንታዊ የሙስሊም ቅዱሣን መቃብሮች እና ሐውልቶች ላይ ጥቃት ደርሷል።

የተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) ተወካዮች ቅዳሜ ዕለት ተሰባስበው የትኛው ቦታ በባህል ቅርጽነት መዘርዝራቸው ውስጥ እንደሚመዘገብ ሲወያዩ አንድ አሳዛኝ ዜና ደረሳቸው። አሳዛኙ ዜና እኢአ ከ1988 ዓም አንስቶ በዓለም ቅርስነት ጥበቃ የሚደረግላት የማሊዋ የቲምቡክቱ ከተማ ላይ ጥቃት መድረሱን ነበር።

In this photo taken Saturday, April 14, 2012, a Tuareg separatist rebel from the NMLA (National Movement for the Liberation of the Azawad) gestures from his vehicle, in a market in Timbuktu, Mali. West Africa's regional bloc is recommending the deployment of a regional force to Mali after Tuareg rebels declared an independent state, dubbed Azawad, following a military coup last month. Regional bloc ECOWAS said Friday, April 13 that the force would help Mali secure its territory and serve as peacekeepers. (Foto:AP/dapd)

የቱዓሬግ አማፂያን አላማ «አዛዋድ» በሚል መጠሪያ እራሷን የቻለች አገር መመስረት ነው።

አንሣር-ዲን በመባል የሚታወቀው አማፂ ቡድን ከአል-ቃኢዳ ጋ የተሳሰረ አክራሪ ቡድን ነው። የቡድኑ ታጣቂዎች የጥንት ታዋቂ መቃብሮች እና ሐውልቶችን በመጥረቢያ እንዳፈረሱ የዓይን ምሥክሮች ተናግረዋል። እንዲሁም ቡድኑ 16 የቅዱሳን መቃብሮች እና ሐውልቾቻቸውን በሙሉ ለመውደም መዛታቸው ተነግሯል። በርካታ በደቡብ ማሊ የሚኖሩ ዜጎች በሰሜን ላሉ ቤተሰብና ዘመዶቻቸው ተጨንቀዋል። አንድ ተቃዋሚ ሰልፈኛ ለዶይቸ ቬለ እንደገለፀው፤ « የማሊ መንግስት ያለበትን ኋላፊነት እንዲወጣ እንፈልጋለን። መንግስት ወደ ጦርነት እንድንዘምት መሳሪያ ሊያስታጥቀን ይገባል። አንድ ራሱን የቻለ የሲቪል ቡድን በማደራጀት ላይ እንገኛለን። በሰሜን ያሉ ወንድሞቻችን በባዶ እጃቸው እየታገሉ ነው ። ዱላ እና ድንጋይ ይዘው ከካላሺንኮፍ መሳሪያ ጋ»

የቲምቡክቱ ከተማ «የበረሀ ዕንቁ» በመባልም ትታወቃለች። ከተማዋ በተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) በቅርስነት እኢአ 1988 ተመዝግባለች። በውስጧ ያሉት ጥንታዊ መስጊዶች እና አብያተ-መፅሐፍት

die 1988 von der UNESCO zum Weltkulturerbe erklärte Moschee von Sankore in Timbuktu mit UNESCO-Schild

የቲምቡክቱ መስጊድ

ሳይቀሩ ስለ ቲምቡክቱ ታሪካዊነት ይመሰክራሉ። ይህም ስፍራ የአገር ጎብኝዎች መስብ ነበር። አሁን ግን የቱዓሬግ አማፂያን እና አንሣር-ዲን የተባለው እስላማዊ አክራሪ ቡድን ከተማይቱን በቁጥጥር ስር አውለዋታል።

የዩኔስኮ ዋና ኃላፊ ኢሪና ቦኮቫ «በባህል ቅርሱ ላይ ለደረሰው ጥቃት ምንም አይነት ነገር ምክንያት ሊሆን አይችልም። የደረሰው ውድመት ይህ ነው የሚባል አይደለም። አንሣር ዲን ጥቃቱን በፍጥነት ማቆም አለበት» ሲሉ አሳስበዋል።

በመዲና ባማኮ የተመሰረተው የሽግግር መንግስት ለመጠናከር ጥረት በሚያደርግበት በአሁኑ ወቅት በሰሜናዊው ማሊ የቱዓሬግ አማፂያን ጥቃታቸውን ቀጥለዋል። አላማቸው፤

«አዛዋድ» በሚል መጠሪያ እራሷን የቻለች አገር መመስረት ነው። የአክራሪ ሙስሊሞቹ ቡድን ከቱዋሬግ ዓማጺያን ጋር አሁን የሰሜን ማሊን ሁለት-ሶሥተኛ ግዛት ተቆጣጥሯል።

ሜቲው ጊውዴር በጄነቭ ዮንቨርሲት የሳህል ጉዳዮች አጥኚ ናቸው። በሲቪሉ ህዝብ ላይ የሚደርሰው ጥቃት በፍጥነት መፍትሄ ሊያገኝ ይገባል ይላሉ። ካለበለዚያ የርስ በርስ ጦርነት መከፈቱ አይቀሬ ነው።

epa03173146 (FILE) A file photograph dated 21 October 2011 shows Tuareg rebel fighters moving through northern Mali on a pick-up truck with a mounted heavy machine gun, near Kidal, Mali. Reports on 06 April 2012 indicate that a Tuareg rebels group known as the National Movement for the Liberation of Azawad (MNLA) in the north of Mali have declared independence for a region they are calling Azawad, after seizing control of the area following their advances southward and in the wake of the 21 March coup. It called on the international community to recognize the new nation and said it would respect the borders of neighbouring states. The UN Security Council on 04 April condemned the rebel attacks in northern Mali and called for an end to the violence. The rebels took the historic city of Timbuktu at the weekend with the help of Islamist groups. EPA/STR

የቱዓሬግ አማፂያን

« ሁሉም አሁን ስለጦርነት እና ስለበቀል የሚናገሩት ሁሉ የስካሁኑ ጦርነቱ ካስከተለው በላይ ሰዎችን ለስደትና ለጉዳት እያጋለጡ ነው። የሚሰደዱ እና የሚጎዱ ሰዎች ይጠብቋቸዋል። ሰሜኑን የሃገሪቱን ክፍል ከያዙት ቡድኖች ጋ በመጀመሪያ ፖለቲካዊ ድርድር ማካሄድ የሚችል የተረጋጋ እና ጠንካራ የሆነ መንግስት ባማኮ ላይ ያስፈልገናል። እንዲህ አይነት መንግስት እስካሁን የለንም። መዲናይቱ ባማኮ እስካልተጠናከረች ድረስ

በአሁኑ ሰዓት ወደ ሰሜን ሄዶ በወታደራዊ ኃይል መፍትሄ መሻቱ አደገኛ ውጤት ሊያስከትል ይችላል። »

ጠንካራ የማሊ መንግስት ስለሌለ በብዙ የቲምቡክቱ ነዋሪዎች አለም አቀፉ ማህበረሰብ ነው ተስፋቸው። በሰሜናዊ ማሊ በተባባሰው ግጭት እና ወንጀል ምክንያት የተባበሩት መንግስታት እንዳስታወቀው 300 000 ሰዎች ቀያቸውን ጥለው ተሰደዋል። አብዛኞቹም በጎረቤት አገሮች ጥገኝነት እየጠየቁ ነው።

ልደት አበበ

ሒሩት መለሰ

Audios and videos on the topic

 • ቀን 02.07.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/15Q8w
 • ቀን 02.07.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/15Q8w