ማሊና የምርጫ ዝግጅቷ፣ | አፍሪቃ | DW | 24.07.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

ማሊና የምርጫ ዝግጅቷ፣

በማሊ አዲስ ፕሬዚዳንት እስኪመረጥ እስከፊታችን እሁድ ጥቂት ቀናት ናቸው የቀሩት። አሁን ጥያቄው ፣ ምርጫው በሀገሪቱ በመላ በሰሜናውያኑ ከተሞችም ይካሄድ ይሆን ወይ ? የሚለው ነው። ምርጫው ከመጀመሩ ጥቂት ቀናት እንደቀሩት የኅይል እርምጃ መከሠቱ ግን ፣ ብሩኅ ተስፋ አላሳደረም ።

በሰሜናዊቷ ከተማ በጋዎ የገበያ አዳራሽ፤ የዋጋ ውጣ -ወረድ ክርክር ይሰማል፤ የሰው ጩኸት ይተማል ገበያውም ደርቷል፣ የመባልእትና የዐቃዎች ዋጋ እጥረት የለም። ሥጋ ሻጩ ነጋዴ፤ ትኩስ የፍየል ሥጋ ያቀርባል። አጠገቡ ፣ የቅመማ -ቅመም ነጋዴዎች የሆኑ ሴቶች ምርታቸውን ኑ! ግዙ ይላሉ። ከኒጀር ወንዝ የተጠመድ ትኩስ አሣ የሚሸጡ ሴቶችም ቦታቸውን ይዘው ገዥዎችን ይጠብቃሉ። አይቻታ ኬይታም በዚሁ ዕለት ተዘዋውረው ሁኔታውን በመመልከት ርካታ ነው የተሰማቸው። እርሳቸውም ፣ በጋዎ ፣ የአሣ ነጋዴዎች ማኅበር ፕሬዚዳንት ናቸው።

2,«ብርቱው ውዝግብ አጋጥሞ በነበረበት ወቅት ፤ ኑሮ በዚህ አካባቢ በጣም ከባድ ነበረ ። ከቻድ በኩል የፈረንሳይ ወታደሮች ወደዚህ ከመጡ ወዲህ ግን፣ ሁኔታዎች ከሞላ ጎደል በመሻሻል ላይ ናቸው። ከዚያ በፊት ተሠቃይተን ነበር። እና ሴቶቹ በተለይ ከቤት እንኳ መውጣት የማንቃጣበት ሁኔታ ነው የነበረው። አሁን ግን ሁኔታዎች እንደገና ተሻሽለውልናል።»

ጋዎ ፤ ከአማጽያን እጅ ነጻ የወጣች ፣ ከ6 ወራት በፊት ነው። ያም ሆኖ የሰሜን ማሊ አዛዋድ ነጻ አውጭ ድርጅትና በኋላም አንድነትና ጂሃድ የተሰኘው ድርጅት በመፈራረቅ በከተማይቱ በአጠቃላይ አንድ ዓመት ያህል የቆዩበት ጊዜ ፤ አሁንም ያከተማ አይመስልም ፤ የፖስታ ቤቱ ና የፖሊስ ጣቢያው ህንጻዎች በተለይ በጥይት ተበሳስተው ነው እስካሁን የሚታዩት።አሁን ግን ቀስ በቀስ ሁሉም እንደሚለወጥ ተስፋ አለኝ አንዱ ተስፋ፣ የእሁዱ የፕሬዚዳንትነት ምርጫ ነው ይላሉ፤ አይቻታ ኬይታ--

3,«ምርጫው በጥሩ ሁኔታ ነው የሚካሄደው። የመምረጫ ካርዴ አለ፤ ኒናንም አምጥቼአታለሁ። ሌሎቹ ሴቶችም የምርጫ ካርዶቻቸውን አግኝተዋል። »

የከተማይቱ ኑዋሪዎች እንዲህ እንዳሁኑ ብሩኅ ተስፋ ሲያንጸባርቁ አልታየም። በሚመጡት ቀናት ከጋዎ በስተሰሜን 350 ኪሎሜትር ራቅ ብላ በምትገኘው ኪዳል ፣ ምን ሊያጋጥም እንደሚችል የሚታወቅ ጉዳይ የለም። በምሬት የሚናገሩት ዕቃ አመላላሽ የከባድ ጭነት ተሽከርካሪ ዘዋሪ ሃሩና ቱሬ ይራገማሉ። አካባቢው ባለፉት ወራት እንደታየው ከሆነ ፈጽሞ ለመበጎብኘት የሚሹት አይደለም። ቱሬ ፣ ከጋዎ- ኪዳል ብዙ ጊዜ ተመላልሰዋል።

4,«በዚያ አካባቢ ሁሉ ሽፍታ ነው።ሁሉም መሣሪያ የተጠቀ ነው። አለቃ የሚባል የለም። እያንዳንዱ አለቃ እንደሆነ ነው የሚሰማው።»

ሃሩና ቱሬ፣ በየመንገዱ ተሽከርካሪ እያስቆሙ ፤ ገንዘብ አምጡ የሚሉትን ለምጄአቸዋለሁ። ያስደነገጠኝ ፣ ከ 6 ቀናት ገደማ በፊት በአዛዋድ ነጻ አውጭ ድርጅትና በከተማይቱ ኑዋሪዎች መካከል በተደረገ ግጭት የተገደሉት 4 ሰዎች ሁኔታ ነው ይላሉ።

ከዚያም ጋር በተጨማሪ ፣ ከአልጀሪያ ጋር በሚያዋስነው ግዛት ፣ በቴሳሊት ፣ በኋላ ቢለቀቁም 6 የምርጫ ረዳቶች ታፍነው ተወስደው የነበረበት ሁኔታ አስደንጋጭ እንደነበረ አልታበለም። በጋዎ ከቤታቸው ወደ ገበያ ይጓዙ የነበሩት ሳፊ ሜጋ የተባሉት ወ/ሮ አንድ ተማጽኖ አላቸው።

5,«የኪዳል ይዞታ መረጋጋት አይታይበትም። የማሊ ጦር ሠራዊት ዝምቶ ኪዳልን መቆጣጠር ይኖርበታል። ኪዳል በቁጥጥር ሥር እስካልዋለች ድረስ በዚህ በጋዎ መኖር አንችልም። በኪዳል፤ እንዲሁም ባጠቃላይ በሰሜናዊው ማሊ ሰላም እንዲሠፍን እንሻለን። በማላ ማሊ ሰላም እንፈልጋለን።»

ዋጋዱጉ ላይ ፤ በማሊ የሽግግር መንግሥትና በ 2 ቱ የሰሜናዊው ማሊ የደፈጣ ውጊያ ድርጅቶች መካከል በተደረገ የሰላም ስምምነት መሠረት ነው፤ ጦር ኃይሉ ወደግዛቶቹ ሁሉ መጓዝ መቻል አለበት። ስምምነቱም ነው ምርጫ እንዲካሄድ መንገድ የጠረገው። ከባድ የጭነት አሽከርካሪ ሃሩና ቱሬ ግን ከተገንጣዩ ድርጅት ጋር በጭራሽ በፍጹም ድርድር አያሻም ነበረ ባይ ናቸው።

«በየዕለቱ ፣ አውቶሞቢሎች 3 ወይም 4 መባልእትና ዕቃ አቅራቢ ተሽከርካሪዎችን የሚሠርቁት እነዚያው የሰላም ስምምነት አደረጉ የሚባሉት ሰዎች ናቸው። ሁሉም ያውቃል ግን የሚናገር የለም።የተጠለፉት ነጮችም ቢሆኑ ፤ በሰሜናዊው ታጣቂ ኅይል ታፍነው የሚወሰዱት ንግድ ለማካሄድ ነው። ለአልቃኢዳ አሳልፈው ነው የሚሸጧቸው። ይህንም ሁሉም ያውቃል። ግን አንድም ስለዚህ ጉዳይ የሚናገር የለም»።

የጋዎ አገረ ገዢ ማማዱ አዳማዲያሎ ጎብኝዎችን ተወብለው ሲያነጋግሩ የሚያነሱአቸው ሰሞናዊ ጉዳዮች የማሊው ምርጫና የፀጥታው ይዞታ ናቸው።እንደብዙዎቹ የከተማይቱ ኑዋሪዎች ሳይሆን እሳቸው በምርጫው ላይ በአጅጉ ነው ብሩኅ ተስፋ ያላቸው።

6,«ሁልጊዜ ስንለው የነበረ ጉዳይ ነው። MNLA በሚል ምህጻር የታወቀው ድርጅት እጅግ ንዑስ ነው። ይህ ንዑስ ድርጅት ማድረግ የሚፈለገው ሲታይ፣ ምርጫውን የሚያበላሽ ድርጊት አይፈጸምም በማለት ፣ ተመሥገን ! እንላለን።

እሁድ በኪዳልም መምረጥ እንደሚቻል ፣ በዚያች ከተማ የተመዘገቡት የከባድ ጭነት አሽከርካሪ ሃሩና ቱሬም ተስፋ ያደርጋሉ።

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic