ማሊና ወታደራዊ ዘመቻዉ | አፍሪቃ | DW | 11.12.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

ማሊና ወታደራዊ ዘመቻዉ

የምዕራብ አፍሪካ መንግስታት ሰሜናዊ ማሊን ከአክራሪ ሙስሊሞች ለማስለቀቅ ይፈልጋሉ። ከአውሮፓም ቢሆን ፈረንሳይ ወታደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ በጽኑ ትፈልጋለች። ሆኖም ግን ዩናይትድ ስቴትስና የተበባበሩት መንግስታት እንደዚህ ዓይነቱ ወታዳራዊ እርምጃ ውጤታማ ስለመሆኑ ይጠራጠራሉ።

In this still frame made from video provided by ORTM Mali TV, Mali's Prime Minister Cheikh Modibo Diarra resigns during a broadcast on state television from Bamako, Mali on Tuesday, Dec. 11, 2012, hours after soldiers who led a recent coup burst into his home and arrested him. (Foto:ORTM Mali TV/AP/dapd) MALI ACCESS OUT

ስልጣን የለቀቁት ጠ/ሚ

የምዕራብ አፍሪካ መንግስታት ሰሜናዊ ማሊን ከአክራሪ ሙስሊሞች ለማስለቀቅ ይፈልጋሉ። ከአውሮፓም ቢሆን ፈረንሳይ ወታደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ በጽኑ ትፈልጋለች። ሆኖም ግን ዩናይትድ ስቴትስና የተበባበሩት መንግስታት እንደዚህ ዓይነቱ ወታዳራዊ እርምጃ ውጤታማ ስለመሆኑ ይጠራጠራሉ። ይህ በዚህ እንዳለ ዛሬ የማሊው ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲቦ ዲያራ ከስልጣን መሰናበታቸው ተሰምቷል። ገመቹ በቀለ ዝርዝሩን ያቀርብልናል።

አፍሪቃ-መር ዓለምአቀፍ የማሊ ተልዕኮ በኢንግሊዘኛው ምህጻር AFISMA፣ መች እንደምጀምር ወይም ከቶውኑ ይጀምር እንደ ሆነ ምንም የሚታወቅ ነገር የለም። ምክንያቱም በሰሜን ማሊ ይካሄዳል ተብሎ ስለታቀደው የአፍሪቃ ሀገራት ወታደራዊ ዘመቻ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ልበሙሉ አልሆነም። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ ባን ኪ ሙን ለፖሊቲካዊ ድርድር ቅድሚያ ሊሰጥ ይገባል የሚል አቋም ይዘዋል፣

«ለፖሊቲካዊ ንግግር ቅድሚያ መሰጠት አለበት። ከዚያም ፍጹም አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ወታደራዊ እርምጃው ሊታሰብ ይገባል። ለዚያም ነው እኔም አፍሪቃ-መር ዓለምአቀፍ የማሊ ተልዕኮ ሊታሰብ ይገባል ብዬ የመከርኩት»#b#

ዋና ጸሐፊው ባን ኪ ሙን ለተባበሩት መንግስታት በሰጡት ሐሳብ መሠረት አፍሪቃ-መሩ ዓለምአቀፍ የማሊ ተልዕኮ እንደሚደግፉ ቢናገሩም የጸጥታው ምክር ቤት ግን እንዲህ ዓይነቱን ጥረት በገንዘብ ከመደገፍ እንዲታቀብ መክረዋል። ሆኖም ግን ያለ ምዕራብ ሀገራት እርዳታ የማሊ ጎረቤቶች ማሊን መደገፍ አይችሉም። እንዲህ ዓይነቱ ወታደራዊ እርምጃ እስከ 500 ሚሊዮን ዩሮ ሊያስወጣ ይችላል።

ባለፈው የፈረንጆች ዓመት በሰኔ ወር የምዕራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ድርጅት ECOWAS 3300 ወታደሮችን ወደ ሰሜናዊ ማሊ ለማዝመትና አክራሪ ሙስሊም አማጺያንን ከቦታው ለማስወጣት ጥያቄ አቅርቦ ነበር። ሆኖም ወታደሮቹ አክራሪ አማጺያኑን መጋፈጥ መቻላቸው አጠራጣሪ ነው።

በአንድ የስዊዘርላንድ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም የጸጥታ ጥናት ባለሙያው ማርኮ ዊስ ከተያዘው የሰሜናዊው ማሊ መሬት ስፋት አንጻር ወታደራዊ እርምጃ ብቻ ችግር ይኖረዋል ባይ ናቸው፣

«ግዛቱ በጣም ሰፊ ነው። ማሊ ትንሽ ሀገር አይደለችም። በዛ ላይ ደግሞ የአየር ጸባዩ ትልቅ ሚና ይኖረዋል። ለECOWASና ከምዕራብ ሀገራት የሚመጡ ወታደራዊ ትጥቆችም ለሁሉም የዓየር ጸባይ እንዲስማማ ተደርጎ አልተሰሩም።»

በርግጥ የአፍሪካ-መር ዓለምአቀፍ የማሊ ተልዕኮን ውጤታማነት የሚያጠራጥር የዓየር ጸባይ ብቻ አይደለም። በያዝነው የፈረንጆች ወር መጀመሪያ ላይ አንሳር ዲኔ የተሰኘው አክራሪ የሙስሊም ቡድንና የቱዋሬግ አማጺያን ከማሊ መንግስት ጋር ለመደራደር መስማማታቸው ተገልጿል። ዋና ጸሐፊ ባን ኪ ሙን፣ የተቃደው ወታደራዊ እርምጃ ምናልባት እየተካሄደ ያለውን ሰላማዊ ድርድር ሊያሰናክል ይችላል ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።

የምዕራብ አፍሪቃ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ECOWAS ግን ወታደራዊው እርምጃ ፈጽሞ የማይቀርና በፍጥነት ሊወሰድ ይገባል የሚል አቋም ይዟል። የኮትዲቯር ፕሬዚዳንት አላሳና ኡዋታራ ወታደራዊ እርምጃው ምናልባትም በአዲሱ የፈረንጆች ዓመት መጀመሪያ ሊጀምር ይችላል ሲሉ ተናግረዋል። የሚጠበቀው ጉዳይ የተባባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታ ምክር ቤት በያዝነው ወር ወታደራዊ እርምጃውን የሚደግፍ ውሳኔ ማጽደቁ ይሆናል። የአፍሪካ ህብረትም ቢሆን እርምጃው እንዲወሰድ በጽኑ ጠይቋል። «ኢኮዋስ»ና የአፍሪካ ህብረት

Soldiers march during the independence day celebrations in Bamako on September 22, 2012. Mali held independence day celebrations with its northern territories under the control of armed Islamist groups. The UN Security Council has called for West African nations to produce a 'feasible and actionable' military plan to retake northern Mali. AFP PHOTO / HABIBOU KOUYATE (Photo credit should read HABIBOU KOUYATE/AFP/GettyImages)

ጦር ሐይሉ

የማሊን ሁኔታ ከተባበሩት መንግስታት በተለየ ሁኔታ ለምን ይመለከቱታል ለሚለው የጸጥታ ጥናት ባለሙያው ማርኮ ዊስ ሲመልሱ፣

«ሁለቱም ECOWASና የአፍሪካ ህብረት ይህን ስፍራ የመቆጣጠር አቅም እንዳላቸው ሊያሳዩ ይፈልጋሉ።»

ወታደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ በአጽንዖት ፍላጎቷን የገለጠች ብቸኛዋ ምዕራባዊ ሀገር ፈረንሳይ ናት። ሆኖም ግን እንደ ተባበሩት መንግስታትና ዩናይትድ ስቴትስ፣ የማሊ ጎረቤቶች፣ አልጂሪያና ቻድም ወታደራዊ እርምጃውን በጥርጣሬ ይመለከቱታል። ምናልባት ግጭቱ ወደ ድንበሮቻቸው ሊሸጋገር ይችላል የሚል ፍራቻ አድሮባቸዋል።ይሕ በንዲሕ እንዳለ የማሊ ጠቅላይ ሚኒስትር ሥልጣን መልቀቅ ዳግማዊ መፈንቅለ መንግሥት እንዳልሆነ የሐገሪቱ ጦር ሐይል አስታወቀ።የማሊ ጦር ሐይል ወደ ፈረንሳይ ሊከበልሉ ነበር ያላቸዉን ጠቅላይ ሚንስትር ቼይክሕ ሞዲቦ ዲራን ትናንት አስሮ ዛሬ ሥልጣን እንዲለቁ አስገድዷቸዋል። ጠይላይ ሚንስትሩ ለመኮብለል ሥለ መፈለጋቸዉም ሆነ ሥለመዘጋጀታቸዉ ጦሩ ሐይሉ ከሰጠዉ መግለጫ በስተቀር በግልፅ የታወቀ ነገር የለም።ጠቅላይ ሚንስትሩ ሥልጣን መልቀቃቸዉን ዛሬ ሲያዉጁ እንዳሉትም ሥልጣን ለመልቀቅ የወሰኑት ለሐገሪቱ ሠላም ሲሉ ነዉ።

ገመቹ በቀለ

ሒሩት መለሰ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች