ማህበራዊ ድረ-ገጾች እና ሀሳብን በነጻ መግለፅ | ባህል | DW | 11.12.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

ማህበራዊ ድረ-ገጾች እና ሀሳብን በነጻ መግለፅ

ማህበራዊ ድረ-ገጾች ሰዎች የግል ሀሳባቸውን በነጻ እንዲገልጹ፣ እንዲወያዩ እና እንዲከራከሩ እድል ፈጥረዋል። ለመሆኑ የኢትዮጵያውያን የማህበራዊ ድረገጾች አጠቃቀም ምን ይመስላል? ሀሳብን በነፃ የመግለፅ መብቱ የት ድረስ ነው?

አውዲዮውን ያዳምጡ። 10:14
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
10:14 ደቂቃ

ሀሳብን በነጻ መግለፅ እና ገደቡ

የተለያዩ የማህበራዊ ድረገጾች ከሌሎች ሰዎች ጋር በዓለም ዙሪያ ሀሳብን ለመለዋወጥ ከፍተኛ እድል ፈጥረዋል። አዳዲስ መረጃዎችን በጥቂት ሰከንድ ውስጥ ማግኘት እና የግል ሀሳብን ለሌሎች ማካፈል ይቻላል።መረጃ ሰጪ እና አስተማሪ መልዕክቶች የሚያስተላልፉ እንዳሉ ሁሉ የዛኑ ያህል ህዝብን የሚያደናግሩ እና የሚያሳስቱ የጥላቻ አስተሳሰቦችን የሚያሰራጩ መልዕክቶችንም የሚፅፉ አሉ። ሆነ ብለው የሀሰት መረጃዎችን ለሌሎች ሲያካፍሉ ወይም በዘር፣ በቀለም እና በሐይማኖት ላይ ስድብ እና አሉታዊ መልዕክቶችን የሚያሰራጩ መመልከት ለማህበራዊ ድረ-ገድ ተጠቃሚዎች እንግዳ ነገር አይደለም። በተለይ ኢትዮጵያን የሚመለከቱ መረጃዎችን በተደራጀ መልኩ መልሰው ለኢትዮጵያውያን ከሚያቀርቡ ድረ-ገዶች አንዱ ድሬ ቱዩብ ነው።

ድሬ ቲዮብ የፌስ ቡክ ገፁ ላይ ብቻ 1,5 ሚሊዮን የሚጠጉ ተከታዮች አሉት። የድሬ ቲዮብ መስራች እና ባለቤት ቢኒያም ነገሱ የኢትዮጵያውያንን ማህበራዊ ድረ-ገጽ አጠቃቀም ለማጤን በቂ እድል አግኝቷል። ድሬ ቱዩብም መሠረታዊ እና ወሳኝ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ውይይት ሲካሂዱ ሀሳብን በነጻ የመግለፅ መብቱን በማያከብሩ ላይ ርምጃ ለመውሰድ የሚገደድበት ጊዜ እንዳለ ገልጾልናል።
ዶይቸ ቬለም በተለየያዩ ቋንቋዎች ባሰናዳቸው የፌስ ቡክ ገጹቹ መረጃዎችን ለተጠቃሚዎቹ ያቀርባል፣ ያወያያልም። ባልደረባዬ እሸቴ በቀለ የገጹን ተጠቃሚዎች እያወያየ አስተያየታቸውንም ሰብሰብ አድርጎ ያቀርባል። እሱስ የኢትዮጵያውያን የማህበራዊ ድረ ገፅ አጠቃቀምን በተለይ የዶይቸ ቬለ ገፅን ተጠቃሚዎች እንዴት ይገልጸዋል? ማህበራዊ ድረ-ገጾችን ለሁለት ከፍዬ ነው የምመለከታቸው የሚለው የዋዜማ ራዲዮ ጋዜጠኛ አርጋው አሽኔስ ሀሳብን በነፃ የመግለፅ መብቱን ተጠቅሞ በአግባቡ መወያየት እና ሀሳብ መለዋወጥ እንዲቻል ምን መደረግ አለበት ይላል?
ዝግጅቱን በድምፅ ያገኙታል።


ልደት አበበ
ሂሩት መለሰ


Audios and videos on the topic