ሚኻኤል ሹማኸር | ስፖርት | DW | 03.01.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ስፖርት

ሚኻኤል ሹማኸር

በከፍተኛ የህክምና ክትትል ሥር ያለው የፎርሙላ አንድ ፈጣን የመኪና እሽቅድድም ሰባት ጊዜ ሻምፕዮን ሹማኽር ዛሬ 45ተኛ ዓመቱን ደፍኗል ። አድናቂዎቹ ዛሬ በተኛበት ሆስፒታል አቅራቢያ ተሰባስበው ልደቱ አስበዋል ።

ጀርመናዊዉ የፎርሙላ አንድ የመኪና ሽቅድድም ሻምፒዮና ሚሻኤል ሹማኸር በደቡባዊ ምስራቅ ፈረንሳይ በሚገኘዉ ማሪየብል የአልፕስ ተራራ የመዝናኛ ስፍራ ከቤተሰቡ ጋ በበረዶ ሸርተቴ ስፖርት በመዝናናት ላይ እያለ አደጋ ደርሶበት ሆስፒታል ከገባ ዛሬ ስድስተኛ ቀን ሆነዉ። በዚሁ አደጋ ጭንቅላቱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት ሹማኸር ሁለት ጊዜ የቀዶ ጥገና ህክምና ቢደረግለትም እስካሁን ራሱን እንደሳተ ነው ። በከፍተኛ የህክምና ክትትል ሥር ያለው የፎርሙላ አንድ ፈጣን የመኪና እሽቅድድም ሰባት ጊዜ ሻምፕዮን ሹማኽር ዛሬ 45ተኛ ዓመቱን ደፍኗል ። አድናቂዎቹ ዛሬ በተኛበት ሆስፒታል አቅራቢያ ተሰባስበው ልደቱ አስበዋል ። ሃኪሞቹ ዛሬ የሰጡት አዲስ መግለጫ ባይኖርም ሹማኽርን የሚያውቁትን የስፖርት ባለሞያዎች አነጋግራ የፓሪሷ ዘጋቢያችን ሃይማኖት ጥሩነህ ተከታዩን ዘገባ ልካልናለች።

ሃይማኖት ጥሩነህ

ኂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic