ሚስጥር አጋላጮች | አፍሪቃ | DW | 03.05.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

ሚስጥር አጋላጮች

ሚስጥር አጋላጮች (Whistelblowers) የመንግሥት፤ የባለሥልጣናት፤ የድርጅት፤የኩባንያ እና የመሳሰሉትን ከሕዝብ የተደበቁ ሚስጥሮችን በማጋላጣቸዉ በየሐገሩ አንዳዴም በዓለም ሕዝብ ዘንድ ይወደዳሉ።የዚያኑ ያክል የሚያጋልጡት ሚስጥር በሥልጣናቸዉ ወይም በገንዘባቸዉ ተፅዕኖ የሚያሳርፉ ወገኖችን በመሆኑ ለከፍተኛ አደጋ የተጋለጡ ናቸዉ።

በብዙዎቹ ሐገራት የሕግ ከለላና ጥበቃ አይደረግላቸዉምም።በዚሕም ምክንያት፤ የዶቸ ቬለዉ ማቲያስ ፎን ሐይን እንደዘገበዉ፤ ሚስጥር አጋላጮች በብዙ ሐገራት ከፍ ያለ ዋጋ ለመክፈል ይገደዳሉ።

ብዙዎች ይወዷቸዋል። ሐይለኞች ይጠሏቸዋል።ፍትሕ ትፈልጋቸዋለች። ሕግ ግን ያሳስር፤ ያሳድናቸዋል።ዩናይትድ ስቴትስን የጦር ግፍ ያጋለጠዉ ወታደር ቼልሲ ማንኒንግ 35 ዓመት እስራት ተከናንቧል።ከማንኒግና ብጤዎቹ የሚያገኘዉን መረጃ ዊኪሊክስ በተሰኘ አምደ መረቡ ለሕዝብ የሚያቀርበዉ ጁሊያን አሳጅ በለንደኑ የኤኳዶር ኤምባሲ እንደተዘጋበት ነዉ።


ዩናይትድ ስቴትስ በድፍን ዓለም የምትፈፅመዉን ሥለላ ያጋለጠዉ የቀድሞ የአሜሪካ ሠላይ ኤድዋርድ ስኖደን ሩሲያ ዉስጥ ስደተኛ ነዉ።የተገደለ፤ደብዛዉ የተጠፋ፤ ከሥራዉ የተባበረዉን ቤቱ ይቁጠረዉ።


ጀርመን ዉስጥ የማይበላ እንስሳ ሥጋን ለሽያጭ እንደሚያቀርብ ኩባንያን አጋልጦ የነበር አንድ ሾፌር በ2007 እንደ ጎርጎርያኑ አቆጣጠር ከያኔዉ የኢኮኖሚ ሚንስትር የወርቅ ሜዳሊያ ተሸልሞ ነበር።ሾፌሩ ከሥራ ሲባረር ግን ዞር ብሎ ያየዉ የለም።ሒሳብ መርማሪ ኤርቪን ቢክሲለር የሠራተኛ ጉዳይ መስሪያ ቤቶች የተዛቡ ስታቲስቲክስ ማወጣታቸዉን በማጋለጡ መስሪያ ቤቱ ሐላፊ ስልጣን ለመልቀቅ ተገድደዋል።ቢክሲለር ግን ባልደረቦቹ «አይንሕ ላፈር» ሥላሉት ታሞ ያለ ዕድሜዉ ጡረታ ወጣ።


ሔሰን ግዛት የግብር ሠብሳቢ መስሪያ ቤት ሙሰኛ ሐላፊዎችን ያጋለጠዉ ሩዶልፍ ሽሜንገር የተከፈተበትን የሥም ማጥፋት ዘመቻ ለማስቆም ክስ መስርቶ ከዓመታት ሙግት በኋላ ፍርድ ያገኘዉ ባለፈዉ ታሕሳስ ነበር።የ2009ኙን (እጎአ) የሚስጥር አጋላጮች ሽልማት ያገኘዉ ሽሜንገር እንደሚለዉ እዉነትን ለማጋለጥ የሚከፈለዉ ዋጋ ቀላል አይደለም።

Jahresrückblick September 2006 Deutschland Gammelfleisch«የተጭበረበሩ ሰነዶችን ወይም ሚስጥሮችን የሚያጋልጡ ዉስጥ አዋቂዎች እኛ ሐገር ከለላ እንደሌላቸዉ ማወቅ አለብን።አጋላጮቹ ሥማቸዉ ይጠፋል፤ ይገለላሉ፤ይኪያኪያሳሉ ከሥራ ይባረራሉም።ማሕበረሰቡ ምን እንደሚፈልግ መጠየቅ አለብን።»


የሚስጥር አጋላጭ-መረብ የተሰኘዉ ማሕበር ሊቀመንበር አነግሬት ፋልተር እንደሚሉት ደግሞ ሚስጥር አጋላጮች እነሱን የሚደግፍና ከለላ የሚሰጥ ሕግ በሌለበት ሐገር መጠንቀቅ አለባቸዉ።

«ለሚስጥር አጋላጮች በቂ የሕግ ከለላና ድጋፍ በሌለበት ሐገር ሚስጥርን ማጋለጥ የሚገጥመዉ አደጋ ከፍተኛ ነዉ።እንዲሕ ከማስጠንቀቅ ሌላ የምናደርገዉ የለም።በሌላ በኩል ግን ለማሕበረሰባችን በጣም ጠቃሚ የሆኑ (የተደበቁ) መረጃዎች አሉ።መረጃዎቹ እንዲጋለጡ ብዙ ሚስጥር አጋላጮች እንዲኖሩ መመኘታችን አይቀርም።ግን በቂ ድጋፍ የላቸዉም።»
የጀርመን ምክር ቤት የሚስጥር አጋላጮችን መብት የሚያስከብር ሕግ እንዲያወጣ የአረንጓዴዎቹ ፓርቲ እንደራሴዎች የዛሬ ሁለት ዓመት ግድም ለምክር ቤቱ ረቂቅ-ሕግ አቅርበዉ ነበር።የፓርቲዉ እንደራሴ ሐንስ-ክርሲቲያን ሽትሮቤለ እንደሚሉት ረቂቁ ሰወስት ክፍሎች ነበሩት።Hans-Christian Ströbele Bundestag NSA Debatte 15.01.2014

እንደራሴ ሐንስ-ክርሲቲያን ሽትሮቤለ

«የመጀመሪያዉ፤ሚስጥር አጋላጮች የምጣኔ ሐብት ችግር እንዳይገጥማቸዉ የሚጠይቅ ነዉ።ሁለተኛዉ፤-የመንግሥት መሥሪያ ቤት ተቀጣሪዎችን (ደሕንነት) ለማስጠበቅ ያለመ ነዉ።ሰወስተኛዉ እና በጣም አስፈላጊዉ ሚስጥር በማጋለጣቸዉ ቅጣት እንዳይጣልባቸዉ መከላከል ነዉ።ይሕ ክፍል የስለላ፤የመከላከያ፤የፀጥታ ሰራተኞችንም ይጨምራል።»
ረቂቁ እስካሁን አልፀደቀም።ለነገሩ ሕግ ባለባቸዉም ሐገራት ሚስጥር አጋላጮች ከፈተና አያመልጡም።ዩናይትድ ስቴትስ የሚስጥር አጋላጮችን መብት የሚያስከብር ሕግ አላት።የፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ መስተዳድር ግን ሚስጥር አጋላጮችን እያደነ ነዉ።

ፎን ሐይን / ነጋሽ መሐመድ

ሒሩት መለሠ

Audios and videos on the topic