ሙዚቀኛ መና ሙሉጌታ | ባህል | DW | 22.06.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

ሙዚቀኛ መና ሙሉጌታ

መና ሙሉጌታ ትባላለች። ዛሬ የራሷን አዳዲስ የሙዚቃ ስራዎች ይዛ በወጣቶች አለም እንግዳ ናት።

Sängerin, Menna Mulugeta. Copyright: Menna Mulugeta Juni, 2012

«ራይንላንድ ፋልስ» ተብላ በምትጠራ የጀርመን ክፍለ ግዛት በተዘጋጀ የዘፈን ውድድር ላይ መና ተወዳድራ አንደኛ የወጣችው ገና የ14 አመት ልጅ ሳለች ነው።

Menna Mulugeta CD Cover

የመና ሙሉጌታ የመጀመሪያ የሙዚቃ አልበም

መና ተወልዳ ያደገችው እዚሁ ጀርመን አገር ነው። ሙዚቃ መጫወት ትወዳለች። ይህንንም ችሎታዋን አዳብራ ስራዎቿን በCD አሳትማ መሸጥ ጀምራለች። መና ማዜም የጀመረችው በልጅነቷ ነው።

«ራይንላንድ ፋልስ» ተብላ በምትጠራ የጀርመን ክፍለ ግዛት በተዘጋጀ የዘፈን ውድድር ላይ ተወዳድራ መና አንደኛ የወጣችው ገና የ14 አመት ልጅ ሳለች ነው። የኪነ ጥበብ ሰዎች ዘፈኖችን አስመስላ መጫወት ብቻ ሳይሆን የራሷን ስራዎችንም ዛሬ ለገበያ አብቅታለች። መና የአርቲስት ሙላቱ አስታጥቄ ዜማን በስራዎቿ ውስጥ አካታለች። ምን እንዳነሳሳት ገልፃልናለች።

«በብዛት የፃፍኳቸው ግጥሞች ከግል ህይወቴ ጋ ይገናኛል።» ትላለች መና ።ብዙውን ጊዜ፤ በቤተ ክርስትያን፤ በሙዚቃ ትርዒቶች፣ ድግሶች እንዲሁም በሌሎች ትላልቅ ዝግጅቶች ላይ እየተገኘች ታዜማለች። እንደገለፀችልን ይህንንም ለብዙ አመታት ከትምህርቷ ጎን ለጎን ለማራመድ ችላለች። የወደፊት አላማዋም በሙዚቃው አለም መቆየት ነው። ስለ ግል ስራዎቿ ያጫወተትንን ማድመጥ ይችላሉ።

ልደት አበበ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic