ሙስና በአውሮፓ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 26.11.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

ሙስና በአውሮፓ

በዓለም ዙሪያ የሚፈፀም ሙስናን የሚያጋልጠው ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል የተባለው ድርጅት በየዓመቱ እንደሚያደረግው ዘንድሮም ሙስና በየአገራቱ የሚገኝበትን ደረጃ የሚያሳይ ሰንጠረዥ አውጥቷል ። በዚሁ መዘርዝር ከአውሮፓ ሀገራት ሙስናን በመዋጋት ረገድ አርአያ የሆኑ ሀገራት የመኖራቸውን ያህል ሙስና የተንሰራፋባቸው እንዳሉም ተጠቁሟል ።

default

«የአውሮፓ ሀገራት ከሞላ ጎደል ውጤታማ እና ንፁህ የህዝብ አስተዳደር ስርዓት ቢኖራቸውም ምንም ዓይነት የሙስና ችግር የለባቸውም ማለት አይደለም ። ምክንያቱም በኛ መመዘኛ የመጨረሻውን ደረጃ ያገኙት ሀገራት ውስጥ የሚካሄዱ ህገ ወጥ ውሎች አካል ከመሆናቸውም በላይ ፈላጭ ቆራጭ አገዛዞችም የሚሰርቁትን ገንዘብ እንዲያሸሹ የሚረዱም ናቸውና ። »

በትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል የአውሮፓ እና የማዕከላዊ እስያ ክፍለ አህጉራዊ ዳይሬክተር ሚክሎሽ ማርሻል

ሂሩት መለሰ ፣ ነጋሽ መሀመድ

ተዛማጅ ዘገባዎች