ሙስሊሞች በጀርመን ፣ ስደተኞች በግሪክ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 25.06.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

ሙስሊሞች በጀርመን ፣ ስደተኞች በግሪክ

በጀርመን ከ3.8 እስከ 4.3 ሚሊዮን የሚደርሱ ሙስሊሞች አሉ ። ጀርመን ቀድሞ ከሚገመተው በአንድ ሚሊዮን የሚልቅ ሙስሊም መኖሪያ ናት ።

default

ሙስሊሞች ፀሎት ሲያደርሱ

ሙስሊሞች በጀርመን

ጀርመን የሚኖሩ ሙስሊሞች ከዚህ ቀደም ከሚገመተው በላቀ ሁኔታ ከጀርመን ህብረተሰብ ጋር ተዋህደው እንደሚኖሩ አንድ የቅርብ ጊዜ ጥናት አስታወቀ ። በጥናቱ መሰረት በጀርመን ከሙስሊሞች ግማሽ ያህሉ የጀርመን ዜግነት የያዙ ሲሆን ከሴቶቹ ሰባ በመቶው ራሳቸውን አይከናነቡም ፤ ወይም ጉፍታ አያደርጉም ። በጥናቱ ጀርመን የሚኖረው ሙስሊም ብዛት ቀድሞ ከሚገመተው እጅግ ልቆ መገኘቱ አስገርሟል።

ስደተኞች በግሪክ

የበርካታ ስደተኞች መጉረፊያ ከሆኑት የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት አንዷ ግሪክ ናት ። የሚመጡብኝ ስደተኞች ከአቅሜ በላይ ሆነዋል ስትል የምታማርረው ግሪክ እጎአ እስከ 2009 መጨረሻ ድረስ ከቀድሞ ጠበቅ ያለ አዲስ የስደተኞች እና የተገን ጠያቂዎች ህግ ተግባራዊ ልታደርግ ነው ። ወደ ሌሎች የአውሮፓ ሀገራት መሸጋገሪያ የሆነችው ግሪክ ስደተኞችን በማሰቃየት ትወቀሳለች ።

ሂሩት መለሰ