ሙርሲና የቀጠለው ተቃውሞ | አፍሪቃ | DW | 26.11.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

ሙርሲና የቀጠለው ተቃውሞ

የግብፅ አስተዳደራዊ ጉዳዮች ፍርድ ቤት የፕሬዝዳንቱ ድንጋጌ እንዲሻር የቀረቡትን ክሶች በሚቀጥለው ሳምንት እንደሚመረምር አስታውቋል ። የግብፅ ዜና አግልግሎት ሜና እንደዘገበው ከ12 የሚበልጡ ተመሳሳይ ክሶች ቀርበዋል ።

የግብፁን ፕሬዝዳንት ሞሐመድ ሞርሲን ድንጋጌ በመቃውም በተካሄዱ ሰልፎች የተገደሉት 2 ግብፃውያን የቀብር ስነ ስርዓት በሺዎች የሚቆጠሩ ግብፃውያን በተገኙበት ዛሬ ተፈፀመ ። በስነ ስርዓቱ ላይ ከፊሉ ሲያነባ ከፊሉ ደግሞ የፍትህ ጥያቄ ሲቀርብ ተሰምቷል ። ዳማንሆር በተካሄደው በአንደኛው የቀብር ስርዓት ላይ የሞርሲ ደጋፊዎችና ተቃዋሚዎች ተጋጭተዋል ። ካለፈው ሳምንት አንስቶ በሞርሲ ደጋፊዎችና ተቃዋሚዎች መካከል በተካሄደው ግጭት 444 ሰዎች መቁሰላቸው ተዘግቧል ። በምርጫ የግብፅ ፕሬዝዳንት የሆኑት የሙስሊም ወንድማማቾች ፓርቲው ሞሐመድ ሙርሲ ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ሥልጣናቸውና

ውሳኔያቸው አንዳችም ህጋዊ ተቃውሞ ሊቀርብበት እንደማይችል ከደነገጉ በኋላ ነበር ህዝቡ ተቃውሞውን ማሰማት የጀመረው ። ፕሬዝዳንት በዚሁ ድንጋጌ ላይ ከሃገሪቱ ከፍተኛ ዳኞች ጋር ይነጋገራሉ ተብሎ ይጠበቃል ። ዘግይቶ በደረሰን ዜና መሰረት የግብፅ አስተዳደራዊ ጉዳዮች ፍርድ ቤት የፕሬዝዳንቱ ድንጋጌ እንዲሻር የቀረቡትን ክሶች በሚቀጥለው ሳምንት እንደሚመረምር አስታውቋል ። የግብፅ ዜና አግልግሎት ሜና እንደዘገበው ከ12 የሚበልጡ ተመሳሳይ ክሶች ቀርበዋል ።

ሒሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ