መፍትሄ የራቀው የኑሮ መወደድ | ኢትዮጵያ | DW | 29.08.2021
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

መፍትሄ የራቀው የኑሮ መወደድ

የችግሩን መንስኤ እና ለማስተካከል የሚበጁ ሃሳቦችን በየጊዜው ባገኙት መድረክ የሚገልጹ የኦኮኖሚ ባለሙያዎች ፤ ጉዳዩን ደጋግሞ መነጋገሪያ ከማድረግ ባሻገር መንግሥት በዚህ ረገድ ምን ጥረት እንዳደረገ እንዲናገር ይጠብቃሉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 31:00

 የዋጋ ንረትና ግሽበት ኢትዮጵያን ወዴት እየወሰደ ነው?

 

የዋጋ ንረት ያስከተለው የኑሮ ውድነት ኢትዮጵያ ውስጥ የብዙሃኑ የዕለት ተዕለት ሕይወት እንዳከበደው ከየአካባቢው የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። መሠረታዊ የሚባሉ ሸቀጦች ዋጋ በየጊዜ ሳያሰልስ ማሻቀቡ፤ የመኖሪያ ቤት ኪራይም ሆነ የመጓጓዣ ዋጋው በተመሳሳይ መወደድ በሸማቹ ማኅበረሰብ ላይ ብቻ ሳይሆን አነስተኛ ነጋዴዎችንም ኑሮ አክብዶታል። የአርቦት እጥረት፤ የውጭ ምንዛሪ ክምችት አለመኖር እንዲሁም ግጭት ጦርነት ያስከተለው አለመረጋጋት ችግሩን ከዕለት ወደ ዕለት እያባባሱት በመሄድ ላይ ናቸው።

የችግሩን መንስኤ እና ለማስተካከል የሚበጁ ሃሳቦችን በየጊዜው ባገኙት መድረክ የሚገልጹ የኦኮኖሚ ባለሙያዎች ፤ ጉዳዩን ደጋግሞ መነጋገሪያ ከማድረግ ባሻገር መንግሥት በዚህ ረገድ ምን ጥረት እንዳደረገ እንዲናገር ይጠብቃሉ። የብር የመግዛት ዋጋ መድከም ላለፉት ከአስር ዓመታት በላይ መንግሥት በሀገሪቱ በገንዘብ ረገድ የተከተለው ፖሊሲ መዘዝ መሆኑን የሚናገሩ የኤኮኖሚ ባለሙያዎች ለዚህ መፍትሄው በዋናነት በመንግሥት እጅ ነው ባይም ናቸው። መፍትሄ የራቀው የኑሮ መወደድ፤ የዋጋ ንረትና ግሽበት ኢትዮጵያን ወዴት እየወሰደ ነው? የዚህ ሳምንት የዶቼ ቬለ መወያያ ርዕሰ ጉዳይ ነው። ውይይቱን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች