መጤና ተዛማች ዝርያዎች (IAS) | ጤና እና አካባቢ | DW | 09.06.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ጤና እና አካባቢ

መጤና ተዛማች ዝርያዎች (IAS)

መጤና ተዛማች ዝርያዎች አንዳንዴም መጤና ተዛማች አረሞች ሲባሊ እንሰማለን። አረም ሲል ተክሎችን ብቻ ይመለከታል። ተክሎቹ እንግዳ በሆኑበት አካባቢ የሚያስከትሉት ችግር ነዉ ይህን ስም ያሰጣቸዉ።

default

ይህን በረሃ ለማለምለም የታሰበዉ መጤ ተክል

ግን እንሰሳትም መጤ የሚሆኑበት ጊዜ አለ። ለምሳሌ በእኛዉ አገር በዝዋይ ሐይቅ ከመጀመሪ ይገኝ የነበረዉ የዓሣ ዓይነትና ዛሬ በብዛት ያለዉ አንድ አይደለም። ነባሩን አዲሱ ዝርያ እየበላዉ ቁጥሩን እንዳመናመነዉ እዚያዉ የሚገኙና ከሐይቁ ጋ ብዙ ዘመን የኖሩ ዓሣ አጥማጆች ይናገራሉ። እዚህ ጀርመን አገርም የዉሻና ድመቶችን ዝርያ ሳይቀር ከሌላ አገር አምጥተዉ በማላመድ አራብተዉና አሳድገዉ ሲያበቁ ዛሬ እነዚያ መጤዎቹ ነባሮቹን ዝርያዎች እየጎዱ መሆኑ ማነጋገር ጀምሯል።

ሸዋዬ ለገሠ