መድኃኒት ተላምዶ የሚያገረሸዉ TB ሕክምና | ጤና እና አካባቢ | DW | 04.07.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ጤና እና አካባቢ

መድኃኒት ተላምዶ የሚያገረሸዉ TB ሕክምና

መድኃኒት በመላመድ ዳግም የሚያገረሸዉን TB በአግባቡ መርምሮ ተገቢዉን መድኃኒት ለታማሚዎች ለመስጠት ኢትዮጵያ ዉስጥ ጥረት እየተደረገ ነዉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:21

የTB መድኃኒት

በተለምዶ ሳንባ ነቀርሳ ተብሎ የሚጠራው TB ከዓለም 22 ት ሃገሮችን የሚያጠቃ ተላላፊ በሽታ ነው ።ከነዚህ ሃገራት አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ በበሽታው ሥርጭት በሦስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች ። በአሁኑ ጊዜ መድኃኒት በመላመድ ዳግም የሚያገረሸዉን TB ለተጎዱ ወገኖች ህክምና ማስጀመሪያ የሚሆኑ ከ30 በላይ ተቋማት መኖራቸዉም በበሽታዉ ዉስብስብ ባህሪያት ምክንያት ሕይወታቸዉ ለአደጋ የሚጋለጠዉን አክሞ ለማዳን እንደሚቻልም ተገልጿል። ይህ ጥረት የታሰበዉን ዉጤት እንዲያስገኝም ዳግም የሚያገረሸዉን TB በአግባቡ ለማከም የሚረዱ መድኃኒቶችን ለማቅረብ እርዳታ ሰጪ ድርጅቶች ቃል መግባታቸዉን የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ በላከልን ዘገባ ጠቅሷል።

ዛሬ ይፋ የሆነ አዘገባ እንደሚያሳየዉ የTB ባክቴሪያን ለይተዉ ማወቅ እንዲችሉ የሰለጠኑ አይጦችን ሳይቲስቶች ወደ ኢትዮጵያ እና ባንግላዴሽ የመላክ ዕቅድ አላቸዉ። በቴክኒዎሎጂ የሚታገዙት አይጦች ሞዛምቢክ እና ታንዛኒያ ዉስጥ ለዚሁ ምርመራ ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳደረጉም ተነግሯል።

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic