መድረክ በአዲስ አበባ ያዘጋጀው ሠልፍ | ኢትዮጵያ | DW | 14.12.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

መድረክ በአዲስ አበባ ያዘጋጀው ሠልፍ

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ በአዲስ አበባ ያዘጋጀው ሠልፍ ዛሬ ከግንፍሌ አካባቢ ተነስቶ 22 አካባቢ በሚገኘው ወረዳ 8 ሜዳ ላይ መጠናቀቁ ተገለጠ።

በሠልፉ ላይ የተለያዩ መፈክሮች የተሰሙ ሲሆን፥ ሠልፈኞቹ ገዢው ፓርቲ ከሥልጣን ለመውረድ ፈቃደኛ ስላይደለ ሕዝቡ በምርጫ ከሥልጣን ሊያወርደው ይገባል ማለታቸውም ተዘግቧል። በሠላማዊ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አባላት ላይ እየተኪያሄደ ያለው እስራት እና ወከባ በአስቸኳይ ይቁም የሚል ጥሪም በሰልፉ ላይ ተላልፏል። ባለፈው ሣምንት ሠማያዊ ፓርቲን ጨምሮ የዘጠኙ ፓርቲዎች ሊያኪያሂዱ ያቀዱት ሰልፍ በፖሊስ የድብደባ እና የእስራት ተግባር መደናቀፉ መሰማቱ ይታወሳል። መድረክ ዛሬ ያኪያሄደው ሠልፍ 10 የአቋም መግለጫዎችን በማሰማት ከቀኑ 7 ሠዓት ገደማ መጠናቀቁን ዘጋቢያችን ከአዲስ አበባ ገልጧል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚያብሄር

ልደት አበበ

Audios and videos on the topic