መዲና በርሊንና ኢትዮጵያዊዉ የአዉቶቡስ ሹፊር | ባህል | DW | 05.05.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ባህል

መዲና በርሊንና ኢትዮጵያዊዉ የአዉቶቡስ ሹፊር

ከ 200 የዓለም ሃገራት የመጡ ማኅበረሰቦች በነፃነት የተለያየ ሃይማኖታቸዉን ባህላቸዉን ይዘዉ የሚኖሩባት ከተማ በርሊን ከጀርመን ርዕሰ ከተማነትዋ በተጨማሪ ከአስራ ስድስቶቹ የጀርመን ግዛቶች አንዷም ናት። ታዋቂ ሙዚቀኞች፤ ዳንሰኞች ግዙፍ መድረክ ላይ ኪነ-ጥበብን የሚያሳዩባት፤ ታዋቂ ሯጮች ረጅም ሩጫን ተወዳድረዉ ስም የሚያተርፉባት ከተማም ናት።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 16:23

መዲና በርሊንና ኢትዮጵያዊዉ የአዉቶቡስ ሹፊር

«በተለይ ወጣቶች አዉቶቡስ ላይ ሲሳፈሩ በጣም ደስ የሚልነዉ አገራችን እንዲህ ተለዉጣ በማየታችን ጥቁር አዉቶቡስ ሲነዳ አይተን አናዉቅም እያሉ ፤ እየተገረሙ ሁሉ የሚያዩ አሉ።»  መዲና በርሊን ሲኖሩ ወደ 24 ዓመት እንደሆናቸዉ የሚናገሩት በከተማዋ የመጀመርያዉ አፍሪቃዊ የከተማ አዉቶቡስ አሽከርካሪ አቶ ኤፍሪም ገብሩ የሰጡት አስተያየት ነዉ።

ከ 200 የዓለም ሃገራት የመጡ ማኅበረሰቦች በነፃነት የተለያየ ሃይማኖታቸዉን ባህላቸዉን ይዘዉ የሚኖሩባት ከተማ በርሊን ከጀርመን ርዕሰ ከተማነትዋ በተጨማሪ ከአስራ ስድስቶቹ የጀርመን ግዛቶች አንዷም ናት። የኦርቶዶክስ የካቶሊክ የፕሮቴስታናንት ፀሎት ቤቶች የተለያዩ መስጊዶች የህንድ እንዲሁም የቡዳ እምነት ቤቶችን ሁሉ አቅፋ የያዘችዉ መዲና በርሊን፤ የዓለም ኮከብ ፊልም አክተሮች፤ ታዋቂ ሙዚቀኞች፤ ዳንሰኞች ግዙፍ መድረክ ላይ ኪነ-ጥበብን የሚያሳዩባት፤ ታዋቂ ሯጮች ረጅም ሩጫን ተወዳድረዉ ስም የሚያተርፉባት ፤ የብሔራዊና የዓለም እግር ኳስ የዋንጫ ግጥምያ የሚካሄድባት የኪነ-ጥበብ የሥነ-ጥበብ እና የባህል ማዕከል ናት። በዚህ ዝግጅታችን የመዲና በርሊን የመጀመርያዉን ጥቁር የከተማ አዉቶቢስ ሹፊርን እየተዋወቅን በርሊን ከተማን እንቃኛለን።  3,5 ሚሊዮን ሕዝብ መኖርያ የሆነችዉ መዲና በርሊን የዓለም ባህል፤ ፖለቲካ እንዲሁም የምዕርምር ማዕከል በመሆንዋ ትታወቃለች።  አስራ ሁለት ቀበሌን የያዘችዉ በርሊን ከተማ «ሽፕሬ» እና «ሃቭል» የተሰኙ ወንዞች በከተማዋ ይፈሳሉ።

በርሊንን የሚያቋርጠዉ ሽፕሬ ወንዝ

የበርሊኒ የከተማ ባቡር

ከተማዋ በ 13ተኛዉ ክፍለ ዘመን በርሊን የሚል በይፋ በመዝገብ ላይ ስያሜን ማግኘትዋ የታሪክ መዝገባት ያሳያሉ። ከተማዋ ጥንት  የብራንድቡርገሮች የፕሮይሶች እንዲሁም የጀርመን መሳፍንታዊ አገዛዝ ማዕከላዊ መቀመጫ እንደነበረች ታሪክ ያሳያል። ከጎርጎረሳዊዉ 1949 ዓ,ም ጀምሮ ደግሞ ከፊል የበርሊን ከተማ የምስራቅ ጀርመን መዲና ሆና ዘልቃለች። ከጎርጎረሳዉያኑ 1961 ዓ,ም ጀምሮ ከተማዋን ለሁለት ምስራቅና በምዕራብ የከፈለዉ በግንብ ተገርስሶ በርሊን ከጎርጎረሳዉያኑ 1990 ዓ.ም ጀምሮ የጀርመን መዲና የዓለም የዓለም ባህል፤ ፖለቲካ እንዲሁም የምዕርምር ማዕከል ሆና ቀጥላለች። በከተማዋ የሚገኘዉን የሽፕሬ ወንዝ ድልድዮችን አቋርጠዉ በመራሂተ መንግሥትዋ መቀመጫና በፓርላማዉ «ቡንደስ ታግ» ሕንጻ በኩል የፕሬዚደንቱ መቀመጫን «ቬሊቪዉ»ን አስታከዉ ከ 172 በላይ የከርሰ ምድር ባቡር ጣብያዎች ላይና ከጣብያዎቹ የሚነሱትን ተሳፋሪዎች ከ25 ሜትር በላይ ርዝመት ያለዉን የከተማ አቶቡስ በማሽከርከር የበርሊንን ነዋሪና እንግዳ ከ 11 ዓመት በላይ በማገልገል ላይ የሚገኙት የመጀመርያዉ ጥቁር አፍሪቃዊ ብሎም ኢትዮጵያዊ አቶ ኤፍሪም ገብሩ የከተማዋን እያንድ ጥግ ጠንቅቀዉ እንድሚያዉቁና ብሎም ለከተማዋ ልዩ ፍቅር እንዳላቸዉ ይናገራሉ።   አዉቶቡስ ነጂ ለመሆን የበቃሁት ይላሉ አቶ ኤፍሪም በመቀጠል፤

ሽሎስ ቤሊቪዉ የፕሬዚደንቱ መቀመጫ

ሽሎስ ቤሊቪዉ የፕሬዚደንቱ መቀመጫ

« እዚህ ጀርመን ከመጣሁ ጀምሮ ራሴ በራሴ ማስተዳደሩን ነበር የምፈልገዉ ፤ የራስን ክብርነት ለማሳየት ያደረኩትም ጥረት ነዉበሌላ በኩልም፤ እድልም የራስም ጥረት አለ። ወደዚህ ስራ የገባሁበት ዋናዉ ምክንያት በአብዛኛዉ ጊዜ አንድ ኢትዮጵያዊ አንድ ስራ ሲይዝ ያንን ተከትሎ ነዉ ስራ የሚይዙት፤ እዚህ በርሊን ዉስጥ ብዙ ታክሲ የሚነዱ ልጆች አሉ ፤ እኔም እንደነሱ ለምን ታክሲ እንዳለሁ እስቲ ሌላ ነገር ልሞክር ብዬ በዚህ ምክንያት አዉቶቡስ ሹፊር ለመሆን አመለከትኩኝ። የመንግሥት መስርያ ቤቱ ማመልከቻዬን ተቀብሎ አይቻልም ለማለት ሞክረዉ ነበር ግን እዚህ አገር ስኖር ብዙ የስራ ዋስት እና ቀረጥ በመክፈሌ ሳይወዱ ፈቀዱልኝ። እንደምንም ብዩ ትምህርቱን ጨርሼ ይህን ስራ ለመጀመር ቻልኩኝ። የዛሩ አስራ አንድ አመት ገደማ ነዉ የከተማ አዉቶቡስን ማሽከርከር የጀመርኩት በከተማዋም የመጀመርያዉ ኢትዮጵያና የመጀመርያዉ ጥቁር አዉቶቡስ ነጂ ነኝ። »    

በበርሊን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ የቅዱስ አማኑኤል ቤተክርስቲያን ጨምሮ መዲና በርሊን ሌሎች  አነስ አነስ ያሉ የኢትዮጵያ ባህላዊ ምግብ ቤቶችና መደብሮችን ሳይጨምር ቤተ-ኢትዮጵያ ፤ ላንጋኖ  እንዲሁም ብሉ ናይል የተሰኙ ባህላዊ ምግብ ቤቶችንም ይዛለች። ከእድሜዬ ብዙዉን ጊዜዬን ያሳለፍኩት በርሊን ከተማ ነዉ ያለን የበርሊኑ የዶቼ ቬለ ጋዜጠኛ ይልማ ኃይለሚካኤል፤ በርሊን ሁሉን እንደፍላጎቱ የምታኖር ከተማ ይላታል።

ራይስ ታግ «የጀርመን ፓርላማ»

ራይስ ታግ «የጀርመን ፓርላማ»

«መቼም  «ሊበራል» ለዘብተኛ ከሚባሉት የዓለም ከተሞች ዉስጥ በኔ እምነት በርሊን ናት። ይህን ይህን የምለዉ እዚህ ስለቆየሁ ብቻ ሳይሆን በርሊን በመሆኑ ብቻ ነዉ። ከሌሎች ከተሞች ጋር ሲነጻፀር  በበርሊን ኑሮ ርካሽ ነዉ። በሕይወቴ ከግማሽ በላይ ያሳለፍኩት በበርሊን ስለሆነ መፀሐፍ መፃፍ እችላለሁ ብዬ አምናለሁ። ግን እኔ እዚህ ከተማ ከመምጣቴ በፊት ከአስር ዓመት ቀደም ሲል ሊሆን ይችላል፤ አፄ ኃይለስላሴ ወደ በርሊን መጥተዉ ትልቅ ንግግር አድርገዋል። ለማስታወስ በዝያ ዘመን ወደ በርሊን የመጡት እኔ አልነበርኩም ነጋድራስ ተሰማ እሸቴ ናቸዉ እኝህ ሰዉ መኪና ለመንዳትና መካኒካል ሥራ ለመማር ነዉ ነጋድራስ ከዝያዉ ጋር አያያይዘዉ የሸክላ ሙዚቃን አስቀርፀዉ በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ መሆኑ ነዉ፤ የታሪክ መዝገባት እንደሚያሳየዉ  ወደ 30 ሺህ የሚሆን ሸክላን አሳትመዉ አዲስ አበባ ወስደዉ ሸጠዉ ትልቅ ሃብት ያፈሩ የከበሩም ሰዉ ናቸዉ።»        

በጀርመን ማንኛዉንም ሥራ ለመሥራት የሞያ ስልጠና ያስፈልጋል። የመጀመርያዉ ጥቁር አፍሪቃዊዉ የከተማ አዉቶቡስ አሽከርካሪ አቶ ኤፍሪም ገብሩ የከተማ አዉቶቡስን ለማሽከርከር ፈቃድ ያገኙት ለወራቶች የዘለቀ ስልጠናን ወስደዉ ነዉ።

« ስልጠናዉ ሰባት ወር ነዉ የፈጀዉ። የከተማ አዉቶቡስ ማሽከርከር ፈቃድ ከመሰጠቱ በፊት ሕግን መማር ያስፈልጋል። ሕግን ያስተምራሉ ሲባል መኪናዉ ማለት አዉቶቡሱ ሲበላሽ ምን ማድረግ እንዳለበት ፤ በአዉራ ጉዳና ላይ አዉቶቡሱን በምን ያህል ፍጥነት ማሽከርከር እንደሚገባ፤ አደጋ ቢያጋጥም ተሳፋሪዉን በጥንቃቄ ቦታ ማስያዝና አዉቶቡሱን ማቆም የመሳሰሉትን ሕግጋቶች ማወቅ ያስፈልጋል።

አሊክሳንደር አደባባይ «የቀድሞዋ ምስራቅ ጀርመን መዲና እምብርት»

አሊክሳንደር አደባባይ «የቀድሞዋ ምስራቅ ጀርመን መዲና እምብርት»

ከዝያ ላይ የኮምፒዉተር ትምህርት ይህ የኮምፒዉር ትምህርት የሚያስፈልገዉ አብዛኛዉ አዉቶቡስ እዚህ ሃገር ከኮምፒዉተር ጋር ተያያዥነት ስላለዉ ነዉ። ከዝያ በኋላ ነዉ ወደ አዉቶቡስ ማሽከርከሩ የገባነዉ። መንጃ ፈቃድ ነበረኝ እንደ አጋጣሚ በኢትዮጵያ ሳለሁ የመኪና ሞተር ስራ ትምህርትን ተከታትዬ ስለነበር ብዙ አልቸገረኝም።»

በጀርመን አንድ ጥቁር የከተማ አዉቶቡስ አሽከርካሪ በዝያ ወቅት የተለመደ አልነበረም ተሳፋሪ አዉቶቡስ ይዘዉ ሲያዮት ምን አይነት አስተያየት ነበር የሚያገኙት?      

« ሰዉ ሁሉ ሲደነግጥ ነበር የማየዉ። አዉቶቡስ እያሽከረከርኩ መኪና በአጠገቤ ሲያልፍ ብራቮ ብለዉ አዉራ ጣታቸዉን ወደላይ እያደረጉ የሚያሳዩኝ፤ እየሳቁ መለስ ቀለስ እያሉ የሚያዩኝ ብዙ ነበሩ። በተለይ ወጣቶች አዉቶቡስ ላይ ሲሳፈሩ በጣም ደስ የሚል ነዉ አገራችን እንዲህ ተለዉጣ በማየታችን ጥቁር አዉቶቡስ ሲነዳ አይተን አናዉቅም እያሉ ፤ እየተገረሙ ሁሉ የሚያዩ አሉ። የዛኑ ያክል በተለይ አዛዉንቶች አዉቶቡስ ዉስጥ ተሳፍረዉ ቀና ብለዉ ሲያዩ ጥቁር ሾፊር መሆኑን ሲያዩ ከአዉቶቡሱ መልሰዉ የሚወርዱ አሉ። አንዳንዶቹ ደግሞ እስቲ ይሄ ጥቁር መንዳት ይችላል ብለዉ ከኋላ ሆነዉ ፍጥጥ ብለዉ እንዴት እንደምታቆም እንዴት እንደምትነሳ እስኪያልብህ ድረስ የሚያዩ አሉ።  በጣም ከብዶኝ ነበር በጀመርኩበት ወቅት። በጎርጎረሳዉያኑ 2006 ዓ.ም ነዉ፤ በበርሊን ከተማ አዉቶቡስ ማሽከርከር ስራን የጀመርኩት። »   

ታሪካዊዉ የበርሊን ስታዲዮም

ታሪካዊዉ የበርሊን ስታዲዮም

 

እና ከመስራቤቶ የሚያገኙት ልዩ ጥቅም ወይም ነገር አለ?

« ብዜ ጊዜ ሌላ ጥቁር አዉቶቡስ ነጂን ለመቅጠር ሲፈልጉ ለማስታወቅያ ብዙ ጎዜ በጋዜጣ ላይ ያወጡኛል። አዉቶቡስ በምነዳበት ሰዓትም ብዜ ጊዜ ሳላዉቀዉ የሊቆጣጠረኝ የሚገባ ሰዉ ይኖራል በጣም ጥንቃቄ የተሞላበት ስራን ነዉ የምሰራዉ። እስከ ዛሬም ምንም አደጋ ደርሶብኝ አያዉቅም፤ እንደዉም ትዝ ይለኛል፤ መስራቤቱ እኔን በማመስገን ከአሜሪካ ሦስት ደብዳቤ ደርሶታል። ከራሽያም እንደዚሁ። ይህ የምስጋና ደብዳቤ ሊመጣ የቻለዉ ቱሪስቶቹ በርሊን በነበሩበት ወቅት እኔ በማሽከረክርበት አዉቶቡስ ዉስጥ ተሳፍረዉ ፤ በቋንቋቸዉ ስላነጋገርኳቸዉና ስለረደኋቸዉ ነዉ።  መስራቤቱ አንዳንድ ከደምወዜ በተጨማሪ ጉርሻን ይሰጠኛል።»     

የዓለም የምርምር ማዕከል በመሆንዋ የምትታወቀዉ የበርሊን ከተማ የተለያዩ ቋንቋ ትምህርት የሚሰጥባትም ከተማ ነች ። የአማርኛና የግዕዝ ቋንቋ ትምህርት በበርሊን ከፍተኛ ተቋም መሰጠት የጀመረዉ በጥንት ጊዜ መሆኑን ጋዜጠኛ ይልማ ኃይለሚካኤል ይናገራል።  

Bundeskanzleramt Flaggen auf Halbmast

የቻንስለር ቢሮ« የመራሂተ መንግስትዋ ቢሮ»

 

« በ 20ኛዉ ክፍለ ዘመን መጀመርያ ላይ ታላቁ ኢትዮጵያዊ ሊቅ አለቃ ታየ፤ አማርኛንና ግዕዝን አስተምረዋል። አጼ ኃይለስላሴ ወደ በርሊን የመጡት በጎርጎረሳዊዉ 1960 ዓ.ም ነዉ። በዝያን ጊዜ በበርሊን ግዜፉ የኦሎምፒያ ስታዲየም ላይ ከኢትዮጵያ ታሪክ ጋር የተገናኘዉንና የኢትዮጵያን የወንጌል የክርስትናን ትምህርት ከሌሎች ቀደም ብለን በጥንት ዘመን እንደሆን በመግለፅ ግሩም ንግግር ማድረጋቸዉ ይነገራል። የበርሊኑ የኦሎምፒያ ስታድዮም ልዩ የሚያደርገዉ ጀሲ ኦን የሚባለዉ የአሜሪካ ሯጭ ስፖርተኛ 1936 ዓ.ም በተካሄደዉ የኦሎምፒክ ጨዋታ ላይ አራት የወርቅ ሜዳልያ በተከታታይ በማሸነፉ እና በዘርኝነት ፖለቲካ በሚያምነዉነዉ በሂትለር ስርአት ሂትለርን አናዶት ከስታድዮም እንዲወጣ ገፍቶታል።  ዓለም አቀፉ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ማኅበር ኢህአፓና መኤሶን ተባብለዉ እንደ ጎርጎረሳዊዉ 1974 ዓ.ም  ተከፋፍለዉ የተለያዩትና የተበታተኑት እዚሁ በርሊን ነዉ። ኢህአፓ የተባለዉ ድርጅት ከሁለት ዓመት ቀደም ብሎ የተመሰረተዉ እዚሁ ሲሆን መኤሶን የተባለዉ ድርጅት ደግሞ  በጎርጎረሳዊ 1968 ዓ.ም ሃንቡርግ ከተማ ላይ ነዉ። ቁቤ የተባለዉን የኦሮሞ ቋንቋ በላቲን ፊደል የመፃፍ ስልት በአቶ ሃይሌ ፊዳ የተነደፈዉና ያስቀመጠዉ በርሊን ከተማና ሃንቡርግ ዩንቨርስቲ ዉስጥ ነዉ። ዓለምን ሊያተራምስ የቻለዉ የኮሚኒስቶች ትምህርትና የፖለቲካ ፍልስፍና የተነሳዉም እነ ማርክስ እነ ኤንግልስም የተማሩት እዚሁ በርሊን ከተማ ነዉ። »    

Deutschland Queen in Berlin bei Gauck Bootsfahrt

በርሊንን የሚያቋርጠዉ ሽፕሬ ወንዝ

 

በርሊን ባህል ማዕከል የሚያሰኛት ጀርመናዉያን የዓለምን ታሪክ መሰብሰብ ማጥናት ስለሚወዱም ነዉ። በርሊን ደግሞ የተሰበሰበዉ ታሪክ መገኛ ናት ሲል ጋዜጠኛ ይልማ ኅይለሚካኤል ገልጾአል። የበርሊንን ጥንታዊ ታሪክም ያየን እንደሆነ እስከ በርሊን ዉህደት ድረስ ቢሆን ታሪካዊ ክስተቶች የታዩባት ከተማ ነች።

« ስለበርሊን ካነሳን ማርክስና ኤንግልስ ብቻ ሳይሆኑ የቦልሸቪክ ሰዎች እዚሁ በርሊን መጥተዉ ድጋፍም አግኝተዉ ገንዘብም ሰብስበዉ ሩስያ ዉስጥ ሊቋቋም የቻለዉን የኮሚኒስቶች ስርዓት እዛዉ ነዉ የመሰረቱት።

Deutschland Multikulturelle Stadt Berlin und der Busfahrer aus Äthiopien

አቶ ኤፍሪም ገብሩ የመጀመርያዉ ጥቁር የበርሊን ከተማ አዉቶቡስ አሽከርካሪ

የበርሊን አጥር ፈርሶም በዘመናቸዉ ከኛ በላይ ሰዉ የለም ብለዉ ይገዙ የነበሩትም የምስራቅ ጀርመኑ እነሆኒከርም ሆኑ ቻቭቼስኮም ሆኑ የፕራግ መሪዉ ፤ በኋላም ከነቭሪዥኔቭ በኋላ ስልጣንን የያዙት እነ ጎርቫቾቭም የወደቁት እዚሁ በርሊን ከተማ ላይ ነዉ። የአሜሪካዉ ፕሬዚዳንት ጆኔቭ ኬኔዲ እኔ ነጻ የበርሊን ዜጋ ነኝ ያሉት እዚሁ በርሊን ላይ ነዉ። ፕሬዚዳንት ሮናልድ ሬገን ጎርባቾቭን እባኮትን ሰዉን የሚከፋፍለዉን ይህን አጥርና ግንብ ያፍርሱት ብለዉ የተጣሩትና ከፋፋዩ ግንብ የተገረሰሰዉ እዚሁ በርሊን ላይ ነዉ። የቅይጥ ባህል ከተማዋን በርሊንና የመጀመርያዉን የበርሊን ከተማ አዉቶቡስ አሽከርካሪ በተመለከተ ሙሉዉን ቅንብር የድምጽ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን እንዲከታተሉ እንጋብዛለን።    

አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሠ

 

 

 

 

 

Audios and videos on the topic