መያዶችን የሚመለከተው የኢትዮጵያ አዲስ ህግ ቅሬታ ማስነሳቱ | ኢትዮጵያ | DW | 07.01.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

መያዶችን የሚመለከተው የኢትዮጵያ አዲስ ህግ ቅሬታ ማስነሳቱ

አሁን በፓርላማ ቀርቦ የፀደቀው ሕግ እንደሚያሳየው፤ በተግባር የሚጨቁን ነው። እናም የሲቪሉ ማኍበረሰብን በመጫን እንደፈለገ ለማድረግ የሚያስችለው መሳሪያ ሊሆን ይችላል...ከጀርባ ያለውን ነገር መመልከት አለብን። በሁለት ሺህ አምስት ግንቦት ላይ ከምርጫው በኋላ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር በምሽት የቴሌቪዥን ንግግራቸው...

ከመያድ ተጠቃሚዎች በከፊል

ከመያድ ተጠቃሚዎች በከፊል

የኢትዮጵያ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፤ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች (መያዶችን) እና ማህበረሰብን የሚመለከተውን ረቂቅ ህግ ትናንት በሰፊ የድጋፍ ድምፅ ማፅደቁ ይታወቃል። ይሕ ህግ ለጋሽ ድርጅቶች በሰብአዊ መብት፣ በፖለቲካ ውይይት እንዲሁም ሴቶችን ተሳታፊ በማድረጉ ረገድ እና በመሳሰሉ ማህበራዊ እንቅሳሴዎች ላይ እንዳይሳተፉ ያግዳል ሲሉ መንግስታዊ ያልሆኑ ሲቪል ማህበረሰባት ቅሬታቸውን በመግለፅ ላይ ናቸው። ከነዚህም መካከል Welt Hunger Hilfe እና Evangelischer Entwicklungsdienst የተባሉ የጀርመን ለጋሽ ድርጅቶች ይገኙበታል። ዽርጅቶቹ እያንዳንዳቸው በዓመት ስምንትና አስራ አምስት ሚሊዮን ዩሮ ቢትዮጵያ ፈሰስ የሚያደርጉ ናቸው።