መዝናኛ፦ እሁድ ታኅሳስ 17 ቀን፣ 2008 ዓ.ም. | መዝናኛ | DW | 27.12.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

መዝናኛ

መዝናኛ፦ እሁድ ታኅሳስ 17 ቀን፣ 2008 ዓ.ም.

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተመልካቾች ያፈራው The daily show የተሰኘው የቴሌቪዥን ዝግጅት ላይ በስላቃዊ ሥራዎቹ ይታወቃል። የአንድ ሰው የመድረክ ላይ ኮሜዲ ሥራዎቹን የጀመረው እንደው በአጋጣሚ መጠጥ ቤት ውስጥ ሞቅ ባለው በአንድ የምሽት አጋጣሚ ነበር።

ዛሬ ከተወለደበት ደቡብ አፍሪቃ አልፎ በምድረ አሜሪካ ዝናው የናኘው ደቡብ አፍሪቃዊ በራሱ ላይ መቀለድም ይወዳል። እንደውም ስለራሱ ሲገልጥ ውልደቱን «ወንጀለኛ ውልደት» እያለ ነው የሚጠቅሰው። ለምን? የዛሬው የመዝናኛ ዝግጅታችን ስለዚህ ኮሜዲያን ማንነት እና ሥራዎቹ ላይ ያጠነጥናል። ዝግጅቱን ናትናኤል ወልዴ አጠናቅሮታል።

Audios and videos on the topic