መዉሊድ ክብረ በዓል | ባህል | DW | 25.01.2013
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

ባህል

መዉሊድ ክብረ በዓል

በዓለም ዙርያ የሚገኙ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች የነብዩ መሃመድ 1487 የትዉልድ ቀንን ዛሪ በደማቅ አክብረዋል። በመዉሊድ ክብረ በዓል ማህበረሰቡ በአንድ ላይ የሚሰባሰብበት ድሆችን የሚያበላበት የሚያለብስበት የሚረዳበት እንዲሁም ወደ አምላኩ የሚጸልይበት ቀን ነዉ። እንኳን ለነብዩ መሀመድ ልደት መዉሊድ በዓል አደረሳችሁ!

በዓለም ዙርያ የሚገኙ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች የነብዩ መሃመድ 1486 የትዉልድ ቀንን ዛሪ በደማቅ አክብረዋል። በመዉሊድ ክብረ በዓል ማህበረሰቡ በአንድ ላይ የሚሰባሰብበት ድሆችን የሚያበላበት የሚያለብስበት የሚረዳበት እንዲሁም ወደ አምላኩ የሚጸልይበት ቀን ነዉ። እንኳን ለነብዩ መሀመድ ልደት መዉሊድ በዓል አደረሳችሁ! መዉሊድ በእስልምና አስተምህሮት ከፈጠሪ ዘንድ የተላኩትና የመጨረሻው ነብይ የሆኑትን የነብዩ ሙሀመድን መወለድ አስመልክቶ የሚከበር በዓል ነዉ ሲል የገለፀልን በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የፍልስፍና ፋክልቲ ሁለተኛ ዓመት ተማሪዉ ወጣት ቶፊክ ባህሩ፣ በሀገራችን የመዉሊድ በዓል አከባበር ነሼዳ በማድረግ በመንዙማ ዚክራ፤ ማለት ለአምላክ ምስጋና በማቅረብ መሆኑን ገልጾልናል። በተለይ በበዓሉ ምሽት ላይ የሚደረገዉ በመንዙማ የሚደረገዉ የምስጋና ማቅረብ ስነ-ስርዓት እጅግ ደማቅ እና ተወዳጅ መሆኑንም ይናገራል። በጥንት ግዜ የመዉሊድ በዓል አከባብርን፤ ከቅርብ ዓመታት አከባበር ስነ-ስርዓት ጋር በማነፃጸርም ቶፊክ አጫዉቶናል። ሌላዉ እድገቱን በኮንቦልቻ እንዳደረገ የገለጸልን ድምጻዊ እድሪስ ሁሴን፤ መዉሊድ በአደገበት በኮንቦልቻ አካባቢ በደማቅ እንደሚከበር በመግለጽ መንዙማ አዚሞልናል። በኢሊባቡር ነዋሪ የሆነዉ ወጣት ኑረዲን ሞሃመድ መዉሊድ በኢሊባቡር እና አካባቢዋ በደማቅ መከበሩን፤ ክብረ በዓሉ ማህበረሰቡ በጋራ በጎሪ ከተማ በሚገኘዉ ስቴዲዮም ዝግጅቱን እንደሚጀምርና፤ በተለያዩ ነብዩ መሀመድን በሚያወድሱ መንዙማዎች ግጥሞች እና አስተምሮቶች ዝግጅቶች እንደሚደረግ ነግሮናል። በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የዓረብ ቋንቋ ትምህርት ክፍል መምህር የሆኑት አቶ ሃሰን ካዎ በበኩላቸዉ መንዙማ በተለይ በመዉሊድ በዓል እንደሚዘወተር ነግረዉናል። መምህር ሃሰን ካዎ በመጀመርያ ይላሉ፤ መንዙማ ማለት ግጥም እንደማለት ሲሆን፤ ቃሉ በራሱ አረብኛ መሆኑን በዝርዝር ነግረዉናል። የመዉሊድን ክንረ በዓል በተመለከተ ያዘጋጀነዉን ሙሉ ቅንብር፤ በዚህ ትንተና ስር የሚገኘዉን የድምፅ መሃቀፍ በመጫን ያድምጡ!

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሃመድ

Audios and videos on the topic

 • ቀን 25.01.2013
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/17QtY
 • ቀን 25.01.2013
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/17QtY