መካ፥ የሟቾች ቁጥር ጨመረ | ዓለም | DW | 26.09.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

መካ፥ የሟቾች ቁጥር ጨመረ

በሳውዲ አረቢያዋ ከተማ መካ አቅራቢያ በምትገኘው በሚና ሐሙስ ዕለት በተከሰተው መጨናነቅ እና ግፊያ የተነሳ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ወደ 769 ከፍ ማለቱን የሀገሪቱ ጤና ጥበቃ ሚንስቴር ዛሬ አስታወቀ።

የሟቾቹ ቁጥር ካለፉት ቀናት በ52 መጨመሩን የተናገሩት የጤና ጥበቃ ሚንስትሩ ካህሊድ አል ፋሊህ ናቸው። ሚንስትሩ በጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ዛሬ እንደተናገሩት ከሆነ ቁጥሩ የጨመረው አደጋው ከደረሰበት ጊዜ አንስቶ በየሐኪም ቤቱ ከገቡት ቁስለኞች መካከል የሞቱት ተደምሮ ነው ። የቁስለኞቹ ቁጥር 934 እንደሆነም የጤና ጥበቃ ሚንስትሩ አክለው ተናግረዋል።

ከሁለቱ የሙስሊሞች ትላልቅ በዓላት አንዱ የሆነዉ የኢድ ዓል-አድሐ በዓል ዘንድሮ ሲከበር ለ1436ኛ ጊዜ ነዉ።

በሙስሊሞቹ ቅዱስ ሥፍራ መካሕና እና አካባቢዉ ሕይወት ያጠፋ አደጋ ሲደርስ ሁለት ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ዉስጥ የሐሙስ ሁለተኛዉ ነዉ።ከአስራ-ሁለት ቀን በፊት በታላቁ የመካሕ መስጂድ ላይ የግንባታ ክሬን ወድቆ ከአንድ መቶ አስር በላይ ሰዎች ሞተዋል።በርካቶች ቆስለዋል።ለዘንድሮዉ ሐጂ 2 ሚሊዮን ያሕል ምዕመን ለዚያራ ተጉዟል።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ልደት አበበ