መኢአድና አንድነት ለመዋሀድ እየተነጋገሩ ነው | ኢትዮጵያ | DW | 16.12.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

መኢአድና አንድነት ለመዋሀድ እየተነጋገሩ ነው

የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲና የመላው ኢትዮዽያ አንድነት ድርጅት ለመዋሀድ ውይይት መጀመራቸውን አስታወቁ። ውይይቱ የተጀመረው በሁለቱ ፓርቲዎች በኩል በተደረገ ንግግር ሲሆን በምርጫ 2002 ምክንያት ውይይቱ በመቋረጡ እንጂ ከጀመሩ ቆይተዋል።

default

የአንድነት የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ አስራት ጣሴ ከቀደመው ስህተት ተምረን ለውህደት ተዘጋጅተናል ብለዋል። ከሁለቱም ፓርቲዎች የተወከሉ ሰዎች እየተነጋገሩ መሆኑንም ጠቅሰዋል። የመላው ኢትዮዽያ አንድነት ድርጅት የውጭ ጉዳይ ሃላፊ አቶ ያዕቆብ ልኬ ውይይቱ መጀመሩን ነገር ግን መግለጪያ ለመስጠት ጊዜው ገና መሆኑን ተናግረዋል። ከባለፈው ስህተት ትምህርት ወስደን ዳግም መፈረካከስ በማይመጣበት መልኩ መነጋገር ጀምረናል ያሉት የሁለቱ ፓርቲዎች አመራሮች ውህደቱ ቢዘገይም ጨርሶ ከመቅረት ግን የሚመረጥ ነው ብለዋል። አንድነት የመድረክ አባል ፓርቲ መሆኑን ያወሱት አቶ አስራት ጣሴ ይህ መሆኑ ከመኢአድ ጋር የሚኖረውን ውህደት እንደማይከለክላቸው ገልጸዋል። ውህደቱን በተመለከተም ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ መረጃው እንደተሰጣቸው ተናግረዋል።

መሳይ መኮንን
ሒሩት መለሰ

Audios and videos on the topic