መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን የሚመለከተው ረቂቅ ህግ መጽደቅ | ኢትዮጵያ | DW | 06.01.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን የሚመለከተው ረቂቅ ህግ መጽደቅ

የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለረጅም ጊዜ ሲያወዛግብና ሲያጨቃጭቅ የቆየውን መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ለመመዝገብና ለማስተዳደር የወጣውን ረቂቅ ህግ ዛሬ በአብላጫ ድምጽ አጸደቀው።

ከኤድስ ጋር የሚኖሩ ህጻናትን የሚረዳ የሚስዮናውያን ድርጅት

ከኤድስ ጋር የሚኖሩ ህጻናትን የሚረዳ የሚስዮናውያን ድርጅት

ወኪላችን ታደሰ እንግዳው እንደዘገበው፡ ምክር ቤቱ ባለፈው ህዳር ሀያ ሶስት ቀን በረቂቅ አዋጁ ላይ ከመከረበት በኋላ ለዝርዝር እይታ ለህግና አስተዳደር፡ እንዲሁም፡ ለማህበራዊና ለውጭ መከላከያና ደህንነት ጉዳይዮች ቋሚ ኮሚቴዎች መርቶት ነበር። በምክር ቤት የተወከሉት የተቃዋሚ ፓርቲዎች እንደራሴዎች ረቂቁ ህግ አሁንም ጉድለት አለው በሚል አልደገፉትም።