1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መንግሥት 125 ኢትዮጵያውያንን ከሊባኖስ መለሰ

ሰኞ፣ ጥቅምት 18 2017

125 ኢትዮጵያውያን ከሊባኖስ ወደ ሃገራቸዉ መመለሳቸዉን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። በርካታ ወጣት ኢትዮጵያዉያት አሁንም ከሊባኖስ መዉጣት እንደሚፈልጉ ታዉቋል። ብዙዎች ህጋዊ ወረቀት እንደሌላቸዉ ነዉ የሚነገረዉ። የአየር ትራንስፖርት ችግር ግን የሥራው እንቅፋት መሆኑ ተመልክቷል።

https://p.dw.com/p/4mK3i
ፎቶ ማህደር፤ በሊባኖስ የቤት ሰራተኛ ኢትዮጵያዊት
ፎቶ ማህደር፤ በሊባኖስ የቤት ሰራተኛ ኢትዮጵያዊት ምስል picture-alliance/AP Photo/G. Kassab

መንግሥት 125 ኢትዮጵያውያንን ከሊባኖስ መለሰ

ትናንት እና ዛሬ 125 ኢትዮጵያውያን ከሊባኖስ ወደ ሃገራቸዉ መመለሳቸዉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። በመካከለኛው ምሥራቅ እየበረታ የመጣውን ጦርነት ትከትሎ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የቆዩ እና ወደ አገራቸው ለመመለስ ሰነድ አሟልተው እና ተመዝግበው የነበሩ 125 ኢትዮጵያውያን ከቤይሩት እንዲወጡ ስለመደረጉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እምባሳደር ነቢያት ጌታቸው ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል።

"ይሄ የማስወጣቱ ሂደት እጅግ ውስብስብ ነው። የአገሪቱ መንግሥት መፍቀድ አለበት" 

"መመዝገብ ብቻ ለመውጣት በቂ አይደለም ያሉት ቃል አቀባዩ ቤይሩት ከሚገኘው  ቆንስላ ጽሕፈት ቤት ጋር በመሆን አሁንም ለችግር ተተጋሉጡ ዜጎችን የማስወጣቱ ሥራ ይቀጥላል ብለዋል። የአየር ትራንስፖርት ችግር ግን የሥራው እንቅፋት መሆኑን አመልክተዋል።

"አንዱ ትልቁ ቁልፍ ችግር የትራንስፖርት ችግር ነው። ሚድል ኢስት ኤርላይን የሚባል ብቻ ነው እየወጣ ያለው። ሌላው ከሰነድ ጋር የተያያዙ ችግሮች ናቸው"

የኢትዮጵያ መንግሥት ሊባኖስ ውስጥ በአስቸጋሪ ሁኔታ ይኖሩ የነበሩ የተባሉ 51 ኢትዮጵያውያንን ከሳምንታት በፉት ወደ አገራቸው መመለሱን አስታውቆ ነበር። ቤይሩት ውስጥ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ጦርነትን በመሸሽ እየተንከራተቱ መሆናቸዉን የሚናገሩ ኢትዮጵያዉያን አስተያየት ሰጭዎች መንግሥት አሁንም በፍጥነት እንዲደርስላቸው እና ካሉበት አስቸጋሪ ሁኔታ እንዲያስወጣቸው በመጠየቅ ላይ መሆናቸዉን የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ሰለሞን ሙጬ ዘግቧል።

ሰለሞን ሙጬ

አዜብ ታደሰ

ዮሃንስ ገብረግዚአብሔር