1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መንግሥት ያደረገውን የኢኮኖሚ ማሻሻያ እንዲሠርዝ መጠየቁ

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 30 2016

መንግሥት በቅርቡ ያደረገውን የኢኮኖሚ ማሻሻያ እንዲርዝ ወይም እንዲከልሰው ኢሕአፓ ጠየቀ። ፓርቲው ዛሬ በሰጠው መግለጫ መንግሥት የዜጎችን ኑሮ የሚጎዳ ያለውን የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) ጎጂ ቅድመ ሁኔታዎች መቀበሉን ኮንኗል። ዉሳኔዉ መንግሥትና ሕዝብን ወደ ከፋ ቅራኔና መፋጠጥ ሊያመጣ ስለሚችል ውሳኔውን እንዲከለስ ጠይቋል።

https://p.dw.com/p/4jAI6
ኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)
ኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)ምስል Solomon Muchie/DW

መንግሥት ያደረገውን የኢኮኖሚ ማሻሻያ እንዲሠርዘው ተጠየቀ

መንግሥት ያደረገውን የኢኮኖሚ ማሻሻያ እንዲሠርዘው ተጠየቀ

 

መንግሥት በቅርቡ ያደረገውን የኢኮኖሚ ማሻሻያ እንዲሠርዘው ወይም እንዲከልሰው የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ጠየቀ። ፓርቲው ዛሬ በሰጠው መግለጫ መንግሥት የዜጎችን ኑሮ የሚጎዳ ያለውን የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) ጎጂ ቅድመ ሁኔታዎች መቀበሉን ኮንኗል። ጦርነት፣ ድርቅ፣ መፈናቀል፣ ቀጣናዊ ለውጦች በበዙበት እና መንቀሳቀስ ፈተና በሆነበት በዚህ ወቅት መንግሥት ይህንን ውሳኔ መውሰዱ "መንግሥት እና ሕዝብን ወደ ከፋ ቅራኔና መፋጠጥ ያመጣል" ሲል ውሳኔው እንዲከለስ ጠይቋል።

 

የፓርቲው ዝርዝር መግለጫ ይዘት

የኢሕአፓ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት መጋቢ ብሉይ አብርሃም ሃይማኖት ያቀረቡት መግለጫ መንግሥት የወሰደው እርምጃ በርከት ያሉ ችግሮች ያሉበት በመሆኑ መንግሥት "ብድርን በሌሌች አማራጮች" እንዲተካ የሚጠይቅ ነው። "የብር ዋጋ ቅናሽ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ውድ ስለሚያደርገው አጠቃላይ የዋጋ ንረትን ያስከትላል፣ የብር ዋጋ ማሽቆልቆል የመግዛት አቅምን ስለሚሸረሽር ለነዋሪዎች ከፍተኛ የኑሮ ውድነት ያስከትላል፣ የኢንቨስተሮችን እምነት ሊያዳክም ስለሚቸል የካፒታልን ወደ ውጭ መፍለስንና ያስከትላል፣ የሀገሪቱን የመከፈል አቅም ይቀንሳል፤ የዕዳ ቀወስ ሊያስከትል ይችላል"

 

መንግሥት መሠል እርምጃዎችን ከመውሰድ ይልቅ መፍትሔው መሬትን የማይሸጥ የማይለውጥ አድርጓል ያሉትን ሕገ መንግሥቱን ማሻሻል፣ የሰዎችን ተዘዋውሮ የመሥራት መብት እና የምርት ዕድገትን ገድቧል ያሉትን "የጎሳ ፌዴራሊዝም" ሥርዓት ማሻሻል ነው ያሉት የኢሕአፓ ፕሬዝዳንት ዝናቡ አበራ የምርት ዕድገትን ማሳደግ እንጅ ብድር አዋጪና ዘላቂ መላ እንደማይሆን ገልፀዋል። ኢሕአፓ መንግሥት "በከፍተኛ ጥንቃቄ የተዘጋጀ" እና ዘላቂ ሀገራዊ ጥቅም ያለው መሆኑን በመግለጽ ተግባራዊ ማድረግ የጀመረውን ይህን የኢኮኖሚ ማሻሻያ እንዲሰርዘው ወይም እንዲያሻሽለው ጠይቋል። የፓርቲው ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ውሳኔው መንግሥት በአለም አቀፍ ደረጃ ተዓማኒነቱን የማጣቱ ማሳያ ነውም ብለዋል። 

ኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)
ኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)ምስል Solomon Muchie/DW

 

"ሀገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ ቀውስ ሊያስከትል ይችላል 

ይህ የመንግሥት እርምጃ የዋጋ ንረትን በከፍተኛ ሁኔታ የሚያባብስ፣ ለጊዜው ማስታገሻ ከመሆን ባለፈ ችግሩን በዘላቂነት ሊፈታ የሚችል የመፍትሔ ሐሳብ አይደለም ሲል ኢዜማ ባለፈው ሳምንት ባወጣው መግለጫ የመንግሥትን እርምጃ ተቃውሞታል። አውዳሚ ጦርነት፣ ውጊያ እና የትጥቅ ግጭቶች፣ መንቀሳቀስ ያለመቻል እና የዕገታ ችግሮች፣ ሕገ ወጥ ንግድ እና የግብር ሥወራ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ የጎላ ተጽእኖ ባሳረፉበት በዚህ ወቅት የተደረገው የኢኮኖሚ ማሻሻያ አወንታዊም አሉታዊም አስተያየት በስፋት እያስተናገደ ይገኛል። የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ዘይት፣ ስኳር፣ ሩዝ እና የስንዴ ዱቄት ጭነው በጉምሩክ ጣቢያ ቆመው የነበሩ  ያላቸውና ገበያውን የሚያረጋጋ ምርት የያዙ 273 ተሽከርካሪዎች ከነተሳቢያቸው የጉምሩክ ሥነ- ሥርዓት ጨርሰው ምርቶችን ማጓጓዝ መጀመራቸው አስታውቃል።

ሰለሞን ሙጬ 

አዜብ ታደሰ 

ሸዋዬ ለገሠ