መንዙማ ምንድን ነዉ! | ባህል | DW | 25.05.2010
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

ባህል

መንዙማ ምንድን ነዉ!

መንዙማ አንዱ የታሪካችን የባህላችን መገለጫ ነዉ። የባህል መድረካችን የያዘዉ ርዕሱ ነዉ። መንዙማ ምንድን ነዉ። ታሪካዊ መነሻዉስ? በእዚሁ ርዕስ ስር ከአስር ቀናት በፊት በአዲስ አበባ ዪንቨርስቲ በኢትዮጽያ ጥናት እና ምርምር ተቋም በርካታ ምሁራኖች

ተማሪዎች እና ባለስልጣናት የተካፈሉበት የሁለት ቀናት አዉደ ጥናት ተካሂዶአል።
ሼህ መሃመድ አወል በመንዙማ እንጉርጉሮዋቸዉ ተወዳጅ እንደሆኑ ይነገራል። በአዲስ አበባ ዪንቨርስቲ ጥናት እና ምርምር ተቋም በአዘጋጀዉ የሁለት ቀናት አዉደ ጥናት ላይ ተካፋይም ነበሩ።፡መንዙማ ምንድነዉ በታሪክ ዉስጥስ ምን ሚና ነበረዉ። ታሪክ ምን ያህል ጥናት ደርጎበታል፣ ይህንን በተመለከቱ ጥያቄዎች እና በተለያዩ ቋንቋዎች የመንዙማ እንጉርጉሮ በአዉደ ጥናቱ ላይ ቀርቦአል፣ የአዉደ ጥናቱ ዋና አዘጋጅ እና በአዲስ አበባ ዪንቨርስቲ መምህር የሆኑት መምህር ከማል አብዱል ዋህር በአዲስ አበባ ዪንቨርስቲ ስለመንዙማ ስለተካሄደዉ አዉደ ጥናት ይገልጹልናል። በሃረር መንዙማ ዝክሪ የሚል መጠርያም አለዉ፣ እንደዉም ዝክሪ የሃደርኛን ቋንቋ ጠብቆ ያቆየ አገር በቀል ተወዳጅ ባህልም እንደሆነ ሌላዋ የአዲስ አበባ ዪንቨርስቲ መምህርት ሃዋአቡበከር ይገልጹልናል! ዝግጅቱን ያድምጡ!

አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic

 • ቀን 25.05.2010
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/17QvT
 • ቀን 25.05.2010
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/17QvT