«መንታ መንገድ» ድራማ ክፍል 3 ገቢር ከ1-26 | በማ ድመጥ መማር | DW | 07.08.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

በማ ድመጥ መማር

«መንታ መንገድ» ድራማ ክፍል 3 ገቢር ከ1-26

ምሕረት ምስጢሯን ለማንም እንዳትነግርባት አስጠንቅቃ ለጓደኛዋ ትእግስት ብታካፍላትም ትእግስት አደገኛ የሚመስለውን መረጃ ጋዜጣ ላይ በማውጣቷ ጓደኝነታቸው ፈተና ይገጥመዋል። ትእግስት የጓደኝነት እምነቷን ብቻ አይደለም ያጎደለችው፤ ይልቁንስ፤ መረጃውን ጋዜጣ ላይ በማውጣቷ የምሕረት ቤተሰቦች አደጋ ይጋረጥባቸዋል።

በእርግጥም ትእግስት ለእዚህ ድርጊቷ ከባድ ዋጋ ትከፍላበታለች። አዲሷ ጓደኛቸው ትንቢት ደግሞ ድብቅ ሕይወት ነው የምትመራው። ከዩኒቨርሲቲ ትምህርቷ ባሻገር በምስጢር የምትከውነው ስራ አላት። ይሁንና ትንቢት ወደ በኋላ ላይ ይኽን ምስጢሯን ለጓደኞቿ ማካፈሏ አይቀርም፤ ጓደኖቿም ወንጀለኛ አለቃዋ ላይ ተባብረው ለመነሳት ድፈረቱን በማግኘታቸው ጉድ ያደርጉታል።

ዳንኤል ምሕረትን ለማየት፥ በእዚያውም ከሦስት ዓመት ሕፃን ልጁ ልዕልት ጋር ቀረቤታ ለመፍጠር በማለም ወደ ኪሲምባ ተመልሶ ይመጣል። ሆኖም ምሕረት በዋናነት ከትእግስት ጋር በገጠማት ችግር የተነሳ፣ እንዲሁም እንደ የልጅ እናት ተማሪነቷ ስኬታማ የምትሆንበትን መንገድ እያሰላሰለች በመሆኗ ዳንኤልን ፊት ትነሳዋለች። ከንጉሤ ጋር የጀመረችው ግንኙነትም ቢሆን ትኩረት የሚሻ ነው። በእዚህም አለ በእዚያ ግን ዳንኤል ኪሲምባ ውስጥ ለመቆየት ይወሰናል። የከባቢ አየርን በማይጎዳ መልኩ ገቢ የሚያገኝበትን መንገድ ያመቻቻል። የከባቢ ጥበቃ ላይ ትኩረት ባደረገው የስራ ዘርፉ የቀድሞ ባላንጣው የንጉሤ እናት፣ ወ/ሮ ዘውዲቱን ሸሪካ ያደርጋል! ለሁለት ሆነውም የንጉሤን እና የምሕረትን ግንኙነት ለማበላሸት ይጥራሉ። ወጣቶቹ ጥንዶች በበኩላቸው የንጉሤን በጠና መታመም ሲረዱ ወደ ጭቅጭቅ የሚመሯቸው ሌሎች ችግሮች ይደቀኑባቸዋል። እንዲያም ሆኖ ታዲያ ጥንዶቹ መጪውን ጊዜ በአንድነት መዝለቅ ይችሉ ይኾን?

Audios and videos on the topic