ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
ይላኩ Facebook Twitter EMail Facebook Messenger Web Whatsapp Web
Permalink https://p.dw.com/p/3nzcs
የሰው ልጅ ሰብአዊ ክብሩ ተገፎ ለካራ የሚጋዝበት የደም መሬት፤ ቤንሻንጉል። ክቡር ገላ በየጢሻው የሚረግፍበት ምድር፤ መተከል። የመቶ ሺህዎች ስጋት እና ሰቀቀን ምንጭ፦ ሕይወት የረከሰበት የኢትዮጵያ ጥግ። በግፍ የታበዩ ጦረኞች የዛር ቆሌያቸው ሲያስጓራቸው ካራቸውን ስለው፤ እንደ እብድ የሚሮጡበት ውድም።
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በንፁሃን ዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው ግድያ እና ዘር ተኮር ጥቃት መንግሥት የክልሉን ሕገ መንግሥት ማሻሻያ ካላደረገበት አይቆምም ሲሉ በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩና ቤተሰብ ወዳጅ ዘመዶቻቸው የተገደሉባቸው የአካባቢው ተወላጆች ለዶይቼ ቬለ ተናገሩ።
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን በሚገኙ ወረዳዎች በንፀሀን ዜጎች ላይ የሚፈፀመው አሰቃቂ ግድያ ትኩረት አላገኘም ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። የክልሉ መንግስት በበኩሉ በመተከል ዞን ሰላምና መረጋጋት ለማስፈን በታጣቂዎች ላይ ርምጃ እየተወሰደ ነው ብሏል።
ከቤንሻንጉል ጉሙዝ መተከል ዞን የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች “በጸጥታ ችግር ምክንያት ወደ አካባቢው መመለስ እንፈልግም” ሲሉ ትላንት እና ዛሬ ተቃውሞ አሰሙ። በአካባቢው አሁንም ሰዎች እንደሚገደሉ ተፈናቃዮች ተናግረዋል። አንድ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኃላፊ በመተከል ዞን አንዳንድ አካባቢዎች አሁንም የጸጥታ ችግር እንደሚስተዋል አምነዋል።