1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መስቀል በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሥር-አማራ

ሐሙስ፣ መስከረም 17 2016

ሰሞኑን ውጊያ የነበረባት በሰሜን ወሎ ዞን የብልብላ ጊዮርጊስ ሀገረስብከት ሰብሳቢ ቄስ ተስፋ አበዋ ደግሞ ምንም እንኳ ህብረተሰቡ ስጋት ቢኖረውም የመስቀል በዓል መከበሩን ተናግረዋል፡፡ በላሊበላ ከተማ ደግሞ ህብረተሰቡ በነቂስ ወጥቶ በዓሉን በድምቀት ማክበሩን የቅዱስ ላሊበላ ሀገረ ስብከት ፀሓፊ ሊቀ ስዩማን መንግስቴ ወርቁ ለዶይቼ አስረድተዋል፡፡

https://p.dw.com/p/4WvHW
በባሕርዳር ከተማ በአሉ ከሞላ ጎደል ተከብሮ ዉሏል
የመስቀል በአል አከባበር በባሕርዳር ከተማምስል Alemnew Mekonnen/DW

የመስቀል በዓል አከባበር በአማራ ክልል


በአብዛኛዉ የአማራ ክልል አስተማማኝ ሰላም የለም።የኢትዮጵያ መንግስት ባለፈዉ ኃምሌ ማብቂያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከደነገገ ወዲሕ የሰዎች እንቅስቃሴ ተገድቧል።የኢንተርኔት አገልግሎት የለም።ስልክም በተወሰኑ ከተሞች ተቋርጧል።የክልሉ ሕዝብ ሠላምና መረጋጋት በራቀበት ድባብ ትናንት መዉሊድና ደመራን ዛሬ ደግሞ መስቀልን አክብሯል።የሥልክና የኢንተርኔት አገልግሎቶች መቋረጥ ዶቸ ቬለን ጨምሮ የተለያዩ መገናኛ ዘዴዎች መረጃዎችን በፍጥነት፣ በዝርዝርና በስፋት ለማቅረብ እንቅፋት ፈጥሮብናል።
የ2016 ዓ ም የደመራና የመስቀል በዓላት ትናንትና ዛሬ በበሕር ዳር ከተማ ተከብሯል፣ የደመራ በዓሉ ትናንተና በባሕር ዳር መስቀል አደባባይ ምዕመናን በተገኙበት በድምቀት ተከብሯል፣ ደመራውን ተከትሎ በየመንደሩ የሚከናወነው የእርድና ተሰብስቦ የማክበሩ ጉዳይ ግን እንደቀደሞቹ ዓመታት ጎልቶ አልታየም፣ ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ ያለው ወቅታዊ የክልሉ ሀኔታ የፈጠረው ድባብ እንደሆነ ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡
በዓሉ በወልዲያ ከተማ በተለየ ድምቀት እንደተከበረ ደግሞ የከተማዋ መጋቢ ጥበበአክሊለ ብርሀን ተመስገን ለዶይቼ ቬሌ በስልክ ገልፀዋል፡፡
ሰሞኑን ውጊያ የነበረባት በሰሜን ወሎ ዞን የብልብላ ጊዮርጊስ ሀገረስብከት ሰብሳቢ ቄስ ተስፋ አበዋ ደግሞ ምንም እንኳ ህብረተሰቡ ስጋት ቢኖረውም የመስቀል በዓል መከበሩን ተናግረዋል፡፡
በላሊበላ ከተማ ደግሞ ህብረተሰቡ በነቂስ ወጥቶ በዓሉን በድምቀት ማክበሩን የቅዱስ ላሊበላ ሀገረ ስብከት ፀሓፊ ሊቀ ስዩማን መንግስቴ ወርቁ ለዶይቼ አስረድተዋል፡፡
የፀጥታ ችግር በማራ ክልል እንዳለ ቢታወቅም የደሴ ከተማ ክርስቲያኖች በጋራ በድምቀት በዓሉን ማክበራቸውን የከተማዋ ሀገረስብከት ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ጠበብት ሲራክ መለሰ አብራርተዋል፡፡
በርከት ያሉ ሐይማኖታዊ በዓላትን በድምቀት ከሚያከብሩ አካባቢዎች አንዷ የጎንደር ከተማ ስትሆን ህፃናት በበዙበት ሁኔታ በዓሉ መከበሩን አንድ የከተማዋ ነዋሪ ገልፀዋል፡፡
የደመራ በዓል በጎንደር ዛሬ ቀን 5 ሰዓት ላይ የቤተክርስቲያናት ሊቃውንት በተገኙበት መከናወኑን ደግሞ የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ በኩረ ትጉሐንዘራ ዳዊት ኃይሉ ተናግረዋል፡፡ ደመራ በጎንደር ሁሌም መስከረም 17 እንደሚከናወን ያመለከቱት ሥራ አስኪየያጁ ይህም የሚሆንበት ህብረተሰቡ በጠዋት በየመንደሩ በግሉ ሲያከብር ስለሚያረፍድ እንደሆነ ገልጠዋል፡፡
ወቅቱ በፈጠረው አሉታዊ ተፅዕኖ ቱሪስት በበዓሉ ላይ እንዳላዩም ተናግረዋል።

ባሕርዳር ዉስጥ በዓሉ በአደባባይ ቢከበርም በየመንደሩ ግን እንደ ወትሮዉ አልተከበረም።
የመስቀል በዓል ባሕርዳር ዉስጥ በተከበረበት ወቅትምስል Alemnew Mekonnen/DW

ዓለምነዉ መኮንን

ነጋሽ መሐመድ

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር