መርዛማዉ የቆሻሻ ክምር በኮት-ዴቮአር | የጋዜጦች አምድ | DW | 06.09.2006
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

የጋዜጦች አምድ

መርዛማዉ የቆሻሻ ክምር በኮት-ዴቮአር

ከዉጭ አገር ምናልባትም ከአዉሮፓ ተጭኖ ኮትዴቮአር፣ አቢጃን መራገፉ የሚነገርለት መርዛማዉ የቆሻሻ ጥርቅም የአገሪዉን ህዝብ ስጋት ላይ መጣሉ ተሰማ።

ባለፈዉ ሓምሌ ወር ኮትዴቮአር፣ አቢጃን ፣ በሶስት ቦታዎች ተቆልሎ የአካባቢዉን ነዋሪ ከፍተኛ የጤና መታወክ ላይ እንደጣለዉም ሲታወቅ በዚሁ የቆሻሻ ክምር ጠንቅ ሁለት ህጻናት መሞታቸዉና ከመቶ በላይ ሰዎች በሆስፒታል ህክምና ላይ እንዳሉ የዶቸ ቬለዋ Meike Scholz ዘግባለች-
የኮትዲቩዋሩ ጋዜጣ የዚህ የቆሻሻ ክምር ብሄራዊ ችግር ነዉ ብሎ ዋና አርስት አድርጎ ዘግቦታል። ኢኮኖሚዉ እንቅስቃሴዉ በደራበት በአቢጃን ከተማ ይህ የቆሻሻ ክምር በአገሪትዋ ላይ ምን ያክል ዉድቀት ሊያመጣ እንደሚችል ግልጽ የሆነ አይመስልም ይላል፣ የአገሪቷ ነጻ ጋዜጠኛ፣ ይመስለኛል እስካሁን ምናልባት ግልጽ የሆነዉ በመርዛማዉ ቆሻሻ ሰዉ ሊሞት እንደሚችል ብቻ ነዉ ይላል በትቸት
«ይህ መርዛማ የቆሻሻ ክምር አሲድማ የሆነ ቫረኪና መሰል ነገር ሲሆን በተለይ ካንሰር ሊያመጣ የሚችል ነገር ሳይሆን አይቀርም ። በጣም ለጤና ጠንቅ የሆነ የአሲድ ነገር ክምር ነዉ»
በተለይ ይህን ጉዳይ በተመለከተ ስሙን ሊጠቅስ ያልፈለገዉ የኮትዲቩዋሩ ነጻ ጋዜጠኛ ጉዳዩ በጣም አሳሳቢ ነዉ ይላል። በከተማዋ አቢጃንም ይህ መርዛማዉ የቁሻሻ ክምር ከዉጭ አገር እንደመጣ ነዉ የሚነገረዉ። ይኸዉም አንድ የፓናማን ሰንደቅ አላምን የሰቀለ የኔዘርላንድ አርማ የተለጠፈበት መርከብ ቆሻሻዉን በከተማዉ ሶስት ቦታዎች አራግፎአል የሚል ነዉ። በዚሁ ምክንያት በከተማዉ ህዝቡ ሰላማዊ ሰልፍ ወጥቶ ነበር ። ከሰላማዊ ሰልፈኞቹ መካከል አንዱ
«ለአሪቷ ፖለቲከኞች በግልጽ የማሳስበዉ ነገር ቢኖር ይህንን የቆሻሻ ክምር እንዲያስነሱ ነዉ። እኛ በከተማዋ የምንኖር ንጹህ አየር መተንፈስ ነዉ ያቃተን፣ እናም ከነገ ዛሪ ነገሩ እየከበደን ነዉ የሚመጣዉ ። እንዴት ነዉ አንድ ሰዉ በዚህ አይነት ሁኔታ ሊኖር የሚችለዉ? አስተዳደር ያለዉ አገር የቆሻሻ ክምር ሲራገፍስ ዝም ብሎ ያያል? ይህ በእዉነቱ ትክክለኛ ነገር አይደለም»
አንድ የአራት እና አንድ የዘጠኝ አመት ሴት ህጻናት በዚሁ ቆሻሻ በመመረዝ ህይወታቸዉን ማጣታቸዉን ከተማዋ ሃኪሞች ከመግለጻቸዉ ሌላ 340 ሰዎች በሆስፒታል በህክምና ላይ እንዳሉ ጨምረዉ አስታዉቀዋል። ሃኪሞቹ ህሙማኑ ላይ ያዩትን ተመሳሳይ የህመም ምልክት ማለትም እንደ የእስትንፋስ ችግር ፣ ነስር እና ተቅማጥ አይነት በሽታ እንደሚሰቃዩም ገልጸዋል።የኮትዴቩዋሩ ነጻ ጋዜጠኛ ህዝቡ ተሸብሮ እና ፈርቶ እንዳለ ነዉ የሚገልጸዉ
«የአገሪቷ ነዋሪዎች ተደናግጠዉ ነዉ ያሉት፣ ለህይወታቸዉም በስጋት ላይ ይገኛሉ። በከተማዉ የበሽተኛዉ ቁጥር እየተበራከተ መምጣቱን እና ትክክለኛ የህክምና እርዳታ የለም ሲል ነዋሪዉ በተለያየ ግዜ በርካታ ሰላማዊ ሰልፍ እና ተቃዉሞ አሳይቶአል።
በኮትዴቮአር እንዲህ አይነቱ ትችት እየተስተጋባ ያለዉ በበሽታ ከተያዘዉ ማለትም ከህመምተኛዉ ብቻ ሳይሆን፣ የአስተዳደሩ ተቃዋሚዎችም በየግዜዉ ችግሩ መፍትሄ እንዲገኝለት ጥሪያቸዉን በማሰማትእ ላይ ይገኛሉ። ሪፑብሊካዉያን የህብረት ንቅናቄ ተብሎ የሚጠራዉ ይህ የተቃዋሚዉ ቡድን መንግስት ለችግሩ መፍትሄ እንደ መፈለግ አፍኖ ይዞታል በሚል ሲከስ፣ በመካከሉ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር Banny በአገራቸዉ አስጊ የሆነ ወረርሽኝ እንደገባ አምነዋል።