መረጃ የማግኘት መብት | ኢትዮጵያ | DW | 06.12.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

መረጃ የማግኘት መብት

መረጃ የማግኘት መብት ኢትዮጵያ ዉስጥ በሕግ ቢደነገግም ተግባራዊ አለመሆኑ ግን ዛሬም የሚያነጋግር ጉዳይ እንዲሆን አድርጎታል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 27:51

መረጃ የማግኘት መብት

መረጃን የመስጠት ኃላፊነት ላይ የተቀመጡ ተጠሪዎች ዘንድ ስለመረጃ ነፃነት አዋጁ ያለዉ ግንዛቤ ዉሱንነትም መረጃን የማግኘት መብቱ በአግባቡ ሥራ ላይ እንዳይዉል እንቅፋት መሆኑን የሚገልፁ አሉ። በሌላ በኩል መረጃን የማግኘት መብትን የሚደነግገዉ አዋጅ በራሱ መረጃን መከልከልን የሚያበረታታ ነዉ በማለት ሕጉ ራሱ እንዲመረመር የሚጠይቁም አሉ። መረጃ የማግኘት መብት በዓለም አቀፍ ደረጃ ስለተደነገገና ተቀባይነት ስላገኘ ብቻ ሳይሆን ከሰብዓዊ መብቶች አንዱ እንደመሆኑ ተግባራዊነቱ እንዴት ሊቀጥል ይችላል? ሊደረጉ የሚገባቸዉ መሻሻሎችስ? ዶቼ ቬለ በዚህ ላይ ዉይይት አካሂዷል። ዉይይቱን ከድምጽ ዘገባዉ ያድምጡ።

ሸዋዬ ለገሠ

ልደት አበበ

Audios and videos on the topic