መልካም አዲስ ዓመት | ኢትዮጵያ | DW | 11.09.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

መልካም አዲስ ዓመት

ኢትዮጵያ የምርጫ ዉጤት ዉዝግብ፤ የእሥራት-ፍርድ ወቀሳ፤ የጉባኤ፤ ጉብኝ መስተንግዶ፤ የኑሮ እና ዉድነት ያጠላበትን ዓመት ልትሰናበት ሠዓታት ሲቀራት፤ ዩናይትድ ስቴትስ ኒዮርክ ላይ በአሸባሪዎች የተገደሉባትን ዜጎችዋን 14ኛ ሙት ዓመት ዘክራለች።አዉሮጶች ያዉ እንደ መሰንበቻቸዉ ሥለስደተኞች መብዛት እያወሩ፤ ሥለመስተግዶዉ እየተነጋገሩ-እየተወዛገቡም ነዉ።የፌስ ቡክ ገፃችን ተከታታዮች ሥለ አሮጌዉና አዲሱ ዓመት የሰጡትን አስተያየት አሰባስበናል። አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ የዶቼቬለ የአማርኛው ክፍል ሃላፊ ሉድገር ሻዶምስኪ ተከታዩን የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላልፈዋል ።
«የተከበራችሁ የዶይቼ ቨሌ አማርኛ አገልግሎት ወዳጆች፤ ለእናንተና ለምትወዷቸው ሁሉ መልካም የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ። በዚህ አጋጣሚ ጥቂት ሰዓታት በቀረዉ 2007 ዓመት ላሳያችሁን አጋርነት ከፍ ያለ ምስጋናዬን ማቅረብ እፈልጋለሁ። በመጪው አዲስ ዓመትም ህልሞቻችሁን፤ ፍላጎታችሁን፤ እንዲሁም ቅሬታዎቻችሁን እያጋራችሁን አብራችሁን እንድትዘልቁ ግብዣዬን አቀርባለሁ። በገፃችን-በራድዮ ሥርጭታችን ላይ የእናንተን አስተያየትና አመለካከቶች ለማካተት ከፍተኛ ጥረት እናደርጋለን። አሁንም በእኛ ላይ ላሳደራችሁት እምነት በድጋሚ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። መልካም አዲስ ዓመት!»

ነጋሽ መሀመድ

ኂሩት መለሰ