መላ ያልተገኘለት የማሊው ድርድር | አፍሪቃ | DW | 05.09.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

መላ ያልተገኘለት የማሊው ድርድር

ካለፈው ሰኞ አንስቶ በአልጀሪያ መዲና በአልጀርስ፤ በማሊ መንግሥትና በሰሜናዊው የአገሪቱ ክፍል በሚንቀሳቀሰው የቱዓሬጎች አማጺ ኃይል ለውዝግቡ መላ ለመሻት ሲካሄድ የሰነበተው ድርድር ሳንክ አጋጥሞታል። ድርድሩ 8 ሳምንታት እንደሚወስድ አስቀድሞ

የተገለጠ ቢሆንም፤ የቱዓሬጎች አማጺ ኃይል፣ የአዛዋድ ብሔራዊ የነጻነት እንቅሥቃሴ በፈረንሳይኛው ምሕጻር (MNLA)ሳምንት ባለሞላ ጊዜ ውስጥ ድርድሩን አቋርጧል። የማሊ መንግሥት በሁኔታው ግራ ተጋብቷል። ቀጣዩ ዘገባ የማሊውን ውዝግብና ድርድር ይዳስሳል።

ባለፈው ግንቦት የቱዓሬግ አማጽያን፤ በኪዳል አካባቢ መጠነ ሰፊ የማጥቃት ዘመቻ ካካሄዱ ወዲህ ¾ኛው የማሊ ግዛት በአማጽያኑ ቁጥጥር ሥር ነው የሚገኘው። የባማኮ ባለሥልጣናት ያላቸው አማራጭ ፣አንድም፣ ቱዓሬጎች ሰፋ ያለ የውስጥ አስተዳደር መብት እንዲኖራቸው መስማማት ፣ አለበለዚያ ከቁጥጥራቸው ውጭ የሆነውን አካባቢው ከአነአካቴው ማጣት ይሆናል። የቱዓሬግ ብሔራዊ ንቅናቄ ቃል አቀባይ ሙሳ አግ አሳሪድ ፣ ለዶቸ ቨለ በሰጡት ቃል ፣ ንቅናቄአቸው ምንጊዜም ለውይይት ዝግጁ መሆኑን ነው የተናገሩት።

«እንደሚታሰበው ቀላል አይደለም። ይሁንና ድርድሩ ይቀጥላል።ድርድሩን የሚያሰናክል ሳንክ አይደለም የተፈጠረው። መስተካከል የሚችል ትንሽ ያለመግባባት ሁኔታ ነው። ዋናውን ጥያቄአችን ማንም ሊረሳው አይገባም፤ አዛዋድ የራሱን ዕድል በራሱ መወሰን ነው የሚሻው።»

በማሊ ሕግና ሥርዓት ገና አልሠመረም፤ ድርድሩ እንደተጀመረ 4 የቻድ ተወላጆች የሆኑ የተባበሩት መንግሥታት ሰላም አስከባሪ ኃይል አባላት ተገድለዋል ። የግድያውን እርምጃ ማን እንደወሰደም አልታወቀም፤ በሰሜን ማሊ፣ እርግጥ ነው፣ ከ 5 በላይ አማጺ ቡድኖች ይገኛሉ። እያንዳንዱ የራሱ ዓላማ ያለው ነው። በባማኮ ዩንቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ ባለሙያ ኢሣ ኢንዲያዬ እንደሚሉት ከሆነ ፣ የእነዚህ ድርጅቶች መለያየት ድርድሩን በጣም የሚያጓትተው ይሆናል። ከ MNLA ከተገነጠለው አንጃ ሌላ ፣ አንሳር ዲኔ የተባለውን ከአል ቃኢዳ ጋር ትሥሥር እንዳለው የተነገረለትን ድርጅት የማሊ መንግሥት በድርድሩ እንዳይሳተፍ አግልሎአል። አንዳንዶቹ ድርጅቶች ደግሞ ለቱዓረጎች የራስን በራስ የመወሰን መብት በፍጹም የቆሙ አይደሉም። በማሊ ጎረቤት በቡርኪና ፋሶ የስልታዊ ጉዳዮች ጥናት ማዕከል ባለሙያ ሙሳ ዑልድ ሄመድ አማር እንዲህ ይላሉ።

«ሰሜን ማሊ ባዙ ንቅናቄዎች የሚንቀሳቀሱበት ቦታ ነው። የሱስ አስያዥ ዕፅ ፤ ሲጋራና ጦር መሣሪያ እንዲሁም ቤንዚን በሕገ ወጥ ንግድ የተስፋፋበት ሁኔታ አለ። ዋናው የአካባቢውና የማሊ ችግር ደካማነት ነው።»የባማኮ ማዕከላዊ መንግሥት፣ ለሰሜኑ የአገሪቱ ከፍለ ሰፋ ያለ ውስጣዊ የአስተዳደር መብት አለመስጠቱን በሺ ኪሎሜትር ርቀት በመዲናይቱ በባማኮ የሚኖሩ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ዜጎች ጥሩ ውሳኔ ባዮች ናቸው።

«ከጥንት ጀምሮ እስከዛሬ፣ የእኛይቱ ማሊ የምትከፋፈል አይደለችም፤

«ሰው በሰው ላይ እምነት ሊጥል ይችላል፤ ግን ፣ እነዚህን ሰዎች አላውቃቸውም፤ እነማን እንደሆኑ አላውቃቸውም። እንዴትስ አምናቸዋለሁ?

«ይህ የሚያሳየው ፣ ሰዎቹ ፣ መፍትኄ ይዞ ለመቅረብ፤ ብሩሕ ተስፋ ያላቸውና ዝግጁዎች መሆናቸውን ነው። »

ማሊ ውስጥ አ ጎ አ በመጋቢት 2012 ዓ ም፤ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ከተደረገ በኋላ፤ የቱዓሬግ አማጽያንና አክራሪ እስላማዊ ታጣቂ ኃይሎች ሰሜናዊውን የአገሪቱን ከፊole በቁጥጥር ሥር ማዋላቸው የሚታወስ ነው። አንሣር ዲኔ የተባለው የእስላማውያኑ አማጽያን ተዋጊ ኃይሎች እንዲያውም ቱዓሬጎችን በማስጨነቅና ወደ ጎን በመግፋት ፣ ወደ መዲናይቱ ባማኮ በመገሥገስ ላይ ነበሩ።

ፈረንሳይ ናት በጥር ወር 2013 በጦር ጣልቃ በመግባት ግሥጋሴአቸውን የገታች! ከዚያም በቡርኪና ፋሶ መዲና በዋጋዱጉ በተደረገ ሥምምነት መሠረት፣ የማሊ የፖለቲካ ድርጅቶችና ፖለቲከኞcve ሁሉ እንደዲመክሩና የፕሬዚዳንት ምርጫ ም እንዲያካሂዱ ተደርጎ፤ ኢብራሂም ቡባካር ኬይታ ርእሰ ብሔር ለመሆን በቁ ። ግን ከዚያን ጊዜ አንስቶ አንዳች የተንቀሳቀሰ ነገር የለም። የጥይት ድምፅ ያልተሰማበት ጊዜም በጣም አጭር ሆኖ ነው የተገኘው። በመሆኑም ጠ/ሚንስትር ሙሳ ማራ፤ ማሊ እንደገና ጦርነት ውስጥ ገባች ሲሉ ማወጃቸው አይዘነጋም። የፈረንሳይ የፖለቲካ ባለሙያና የማሊ ጉዳዮች ተመራማሪ ሚሸል ጋሊ---

«የቱዓሬጎች ንቅናቄ፤ ከሰሜን ማሊ ከተማ ከኪዳል ተነስቶ ወደ ሌሎች የአካባቢ ከተሞች ከመዛመቱም የራሱን መስተዳድር ዘርግቷል። ኪዳልንና አካባቢውን መልሶ ለመቆጣጠርና የመንግሥት ጦር ያደረገው ጥረት ከሽፎበታል። ማሊ ለሐርነት እንዋጋለን ከሚሉ ኅይሎች ያነሰ ሠራዊትና ጦር መሣሪያ ነው ያላት። »

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic