መሃይምነት ድራማ ክፍል 2 -የልእልት የትምህርት ክፍያ ማን ይሸፍንላት ይሆን? | በማ ድመጥ መማር | DW | 15.04.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

በማ ድመጥ መማር

መሃይምነት ድራማ ክፍል 2 -የልእልት የትምህርት ክፍያ ማን ይሸፍንላት ይሆን?

ይህ በመሃይምነትና በትምህርት ላይ የሚያጠነጥን ነው ክፍል 2 ዝግጅታችን ነው፡፡ የዛሬው ጭውውት ሴት ልጅ ትማር²የሚል ርእስ አለው፡፡

የስምንተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመውሰድ  6 ወራት ብቻ የቀራት ልእልት በትምህርቷ ጎበዝ በመሆኗ አንድም ጊዜ ክፍል ደግማ አታውቅም፡፡ ወላጆቿ የተሻለ ትምህርት እንድታገኝ በግል ትምህርት ቤት ገንዘብ እየከፈሉ እያስተማሯት ቢቆዩም በንግድ ስራቸው በደረሰባቸው ኪሳራ የትምህርት ክፍያዋ መክፈል ተስኗቸዋል፡፡ በመሆኑም ትምህርቷን  እንድታቋርጥ የወሰኑትን ውሳኔ ልትታገለው ወስናለች፡፡ እናቷ ይህን ውሳኔያቸውን ከነገሯት ጊዜ አንስታ እንደሷ ሆኖ የሚያግዛት ፍለጋ ላይታች ስትንከራተት ነው የሰነበተችው፡፡ አሁን በጣም የምትወዳት ጓደኛዋ ዙሪያሽን ስላጋጠማት ችግር ልታወራት ቀጠሮ ይዛለች፡፡ ዙራያሽ ገና በ20 ዓመቷ በአንድ ትልቅ የአስጎብኚ ድርጅት ተቀጥራ የምትሰራ ልጅ ናት፡፡

የልእልት የትምህርት ክፍያ ማን ይሸፍንላት ይሆን? እስቲ የዛሬውን ክፍያ ሁለት ጭውውት ተከታተሉ፡፡

Audios and videos on the topic