ሕገ ወጥ ግንባታና የመሪት ወረራ በድሪደዋ  | ኢትዮጵያ | DW | 26.03.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ሕገ ወጥ ግንባታና የመሪት ወረራ በድሪደዋ 

ፕላንን መሰረት ባደረግ ዘመናዊ አመሰራረቷ ትታወቅ ለነበረችው ድሬደዋ የታሪክ ምስክር ሆነው ከቆዩት ነባር መንደሮቿ ውጭ ያሉት መዳረሻዎች በሙሉ ያንን የቀደመ አሻራ አይገልፁም ፡፡ አስተዳደሩ ዛሬም ይሄን እያለ ባለበት በዚህ ጊዜ በአንድ ቀን ዕድሜ ያውም ምሽቱን ብቻ በመጠቀም ተሰርተው የሚያድሩ ግንባታዎች ቁጥር በርካታ ነው ፡፡

ፕላንን መሰረት ባደረግ ዘመናዊ አመሰራረቷ ትታወቅ ለነበረችው ድሬደዋ የታሪክ ምስክር ሆነው ከቆዩት ነባር መንደሮቿ ውጭ ያሉት መዳረሻዎች በሙሉ ያንን የቀደመ አሻራ አይገልፁም ፡፡
ምክንያቱ ደግሞ ከከተማዋ መግቢያ ጀምሮ መስፋፊ በሆኑና በዙርያዋ ባሉ ለአሰፋፈር ምቹ አስካልሆኑ ተራራማ ቦታዎች በህግወጥ መንገድ ለአመታት ሲገነቡ ዛሬን የዘለቁት ሰፈራዎች መልክ ማሳጣታቸው ነው፡፡ የአስተዳደሩ መሬት ልማት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ደራራ ሁቃ ዛሬ ላይ ጫፍ ደርሷል ባሉት ህገወጥነት የተገነባ ግንባታ እስከ ሃያ ሺህ ሲገመት ለችግሩ መባባስ ዋንኛ ካሏቸው ምክንያቶች ደግሞ መንግስት ቦታ አዘጋጅቶ መስጠት አለመቻሉ እና በተለይ በህገወጥ መሬት ወረራው አመራሩ ተሳታፊ መሆኑ ነው ፡፡ሀላፊው  መልካም ትምህርትን ከመሪዎቹ ያጣው ህዝብ ልክም ባይሆን እና ቢያስጠይቅም ድርጊቱን ግን ቀጥሎታል ፤ በተለይ በሀገሪቱ ከለውጥ ጋር በተያያዘ የተፈጠረው ግርግር ሌላ ምቹ ሁኔታን ፈጥራል ፡፡ከሁሉ ባለፈ ግን በአስተዳደሩ የህግ የበላይነትን  በአግባቡ ማስከበር አለመቻሉ ችግሩን አባብሶታል ፡፡የአስተዳደሩ መሬት ልማት ቢሮ ሀላፊ እንደሚሉት ቢዘገይም ለችግሩ መፍትሄ ለመስጠት ጥረት ተጀምሯል ፡፡በአስተዳደሩ ካቤኔ ተገቢ ውሰኔ ማሳለፍ የሚረዳ ጥናት እየተጠና መሆኑንና ይህም ከ2003 ዓ.ም - እስከ 2010 ዓ.ም ድረስ ያሉ ግንባታዎችን የሚያካትት እና በዚያው ጊዜ ላሉት መፍትሄ የሚሰጥ ነው ብለዋል፡፡ሀላፊው እንደተነናገሩት ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ እከ ዛሬም ድረስ በመገንባት ላይ የሚገኙት ግንባታዎች እንዲፈርሱ እና ድርጊቱን የፈፀሙ አካለትም እንዲጠየቁ የማድረግ ውሳኔ መተላለፉን አስረድተዋል ፡፡አስተዳደሩ ዛሬም ይሄን እያለ ባለበት በዚህ ጊዜ በአንድ ቀን ዕድሜ ያውም ምሽቱን ብቻ በመጠቀም ተሰርተው የሚያድሩ ግንባታዎች ቁጥር በርካታ ነው ፡፡ይሄ ደግሞ የአስተዳደሩ ጥረት ሰምሮ የከተማይቱ የፕላን ከተማነት ታሪክ መቼ ይመለሳል የሚለውን መሰረታዊ ጉዳይ ጥያቄ ውስት የሚከት መሆኑን ብዞች ይስማሙበታል ፡፡


መሳይ ተክሉ

 
አዜብ ታደሰ 
ኂሩት መለሰ 

ተዛማጅ ዘገባዎች