ሕገ-ወጥ አዳኞች (ገቢር 3 ትዕይንት 1 እና 2) | በማ ድመጥ መማር | DW | 23.05.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

በማ ድመጥ መማር

ሕገ-ወጥ አዳኞች (ገቢር 3 ትዕይንት 1 እና 2)

ወንጀል ተፋላሚዎቹ! አዲስ ተከታታይ ድራማ ጽሑፍ በፌስ ቡክ። በፈጣን የሴራ ፍሰት፥ በአጫጭር ትእይንቶች የተገነባው ድራማ በአይነቱ ለየት ያለ ነው። ይኽ የድራማ ጽሑፍ በዶይቸ ቬለ የአማርኛው ክፍል የፌስቡክ ገፅ የሚቀርብ ሲኾን፤ ለሽልማት የሚያበቃ ነው። ስለ ተሳትፎ እና ውድድሩ ፌስቡክ ገጻችን ላይ በዝርዝር ይገኛል።

ሕገ-ወጥ አዳኞች (ገቢር 3 ትዕይንት 1)

ሙና የወንድሟ ጳውሎስ ድንገት በሰው እጅ ማለፍ ልቧን አድምቷታል። ባዶ ቤት ውስጥ ዘግታ እየተንሰቀሰቀች ነው። የእጅ ስልኳ ይጠራል።

«ሃይ ሙና! እንዴት ይዞሻል?»

«ምን የምሆን ይመስልሃል ዓለሙ! ያው ወንድሜን እንደሆነ ሉሲ ገድላዋለች።»

«ሙና ስለሱ ገና ምንም አላረጋገጥንም። ወንድምሽን በማጣትሽ በጣም አዝናለሁ። ለቅሶ እና እምባ ግን አይመልሰውም! እመኚኝ ገዳዩን አንጠልጥዬ ለፍርድ እንደማቀርበው ቃል እገባልሽላሁ።»

«ማድረጉ እንደመናገሩ ቀላል ቢሆንማ ምን ነበረበት!»

መርማሪ ዓለሙ እንደቃሉ የወንድሟን ገዳይ ማንንነት ይደርስበት ይኾን?

***  

ሕገ-ወጥ አዳኞች (ገቢር 3 ትዕይንት 2)

በሀገሪቱ የዝኆኖች ቁጥር መመናመን የብዙዎች መነጋገሪያ ኾኗል። በሕገወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የተወረሱ በርካታ የዝኆን ጥርስ ክምችቶችም ተቃጥለዋል። እሳቱን የለኮሱት የበዓሉ የክብር እንግዳ ዶ/ር ሰናይት ናቸው። የሕገወጥ አዳኞቹ መሪያቸው «ሚስተር ጂ» ከመባሉ ውጪ እነማን እንደሆኑ ፍንጭ አልተገኘም። ዶ/ር ሰናይት ንግግር ሲያሰሙ መርማሪ ከበደ ሙሳ ከተባለ ሰው ጋር ይተዋወቃል። ሙሳ የዝኆን ጥርስ ክምችቶቹ ሲቃጠሉ መመልከቱ በጣም አበሳጭቶታል።

«ምንድን ነው ግን ይህን ያኽል ያበሳጨኽ?»

«ምን መሰለህ፤ እኔ ተፈጥሮን እየተዟዟርኩ ፎቶ አነሳለሁ»   

«እኔ ደግሞ መርማሪ ፖሊስ ነኝ። በጸረ ሕገወጥ አደን ክፍል ውስጥ ነው የምሠራው። ቆይ ግን ደኑ ውስጥ ስትዘዋወር አንድም ጊዜ ሕገወጥ አዳኝ ገጥሞህ አያውቅም?»

«ይቅርታ አንዴ ስልክ ላናግር። ሄሎ ቤቲዬ...እየመጣሁ ነው። ይቅርታ መርማሪ መሄድ አለብኝ።»

መርማሪ ከበደ በበዓል አከባበር ሥነ-ስርዓቱ ላይ የሆነ ፍንጭ ባገኝ ብሎ ዐይኑን ያማትራል። ሙሳ ደግሞ ባዶ ቤት ታቅፋ ወደምትጠብቀው ፍቅረኛው በፍጥነት ገስግሷል።

***  


የድራማውን ቀዳሚ ክፍል ማለትም ገቢር 2 አራት ትእይንቶች ይኽን ሲጫኑ ያገኛሉ

 

ጀምስ ሙሃንዶ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ተስፋለም ወልደየስ

DW.COM