ሕገወጥ ሰዉ አሸጋጋሪዉ መኮብለል | ኢትዮጵያ | DW | 09.06.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ሕገወጥ ሰዉ አሸጋጋሪዉ መኮብለል

ወደአዉሮጳና አሜሪካ እወስዳችኋለሁ በማለት ከ80 በላይ ኢትዮጵያዉያንን 20ሚሊዮን ብር አጭበርብረዋል የተባሉ ግለሰብ ከሀገር መኮብለላቸዉ ተሰማ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:52

ሕገወጥ ሰዉ አሸጋጋሪዉ መኮብለል

ግለሰቡ አቶ ሳሙኤል ቦጋለ የሚባሉ ሲሆን ገንዘቡን ይዘዉ ዱባይ እንደነበሩ በአሁኑ ሰዓት ደግሞ ኒዉዮርክ እንደሚገኙ ተበዳዮች መግለፃቸዉን የአዲስ አበባዉ ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር በላከዉ ዘገባ ጠቅሷል። በሕገወጥ መንገድ ሰዎችን ከሀገር ሀገር በሚያዘዋዉሩ ላይ መንግሥት ጠበቅ ያለ ርምጃ ለመዉሰድ የሚያስችለዉን እያወጣሁ ነዉ ባለበት በዚህ ወቅት ግለሰቡ በኢንተርፖል ይመጣሉ እየተባለ ጭራሽ ኒዉዮርክ መግባታቸዉን በመስማታቸዉ ቅሬታ እንዳደረባቸዉ ተበደልን የሚሉት ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።

ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic