ሕይወት እምሻው በፌስቡክ | ባህል | DW | 06.02.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ባህል

ሕይወት እምሻው በፌስቡክ

ሁላችንም ከልጅነት አንስቶ የምናስታውሳቸው ፤ አስቂኝ፤ አሳዛኝ ወይም አስገራሚ ገጠመኞች አሉን። እነዚህን ታሪኮች ግን ስንቶቻችን ዋጋ ሰጥተን፤ በቃላት አስውበን ወረቀት ላይ እናሰፍራቸዋለን። ከትምህርት ቤት ዘመኔ አንስቶ መፃፍ ያስደስተኝ ነበር የምትለው ሕይወት እምሻው፤ በትርፍ ጊዜዋ አጫጭር ታሪኮች እየፃፈች የብዙዎችን ትውስታ ቀስቅሳለች።

አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኝ አንድ - ኤም ኤስ ኤች በሚባል መንግሥታዊ ባልሆነ ድርጅት ውስጥ የጤና ዘመቻ አስተባባሪ ሆና የምታገለግለው ሕይወት፤ ትርፍ ጊዜዋን የምታሳልፈው ድርሰቶችን፣አጫጭር ታሪኮችን በመፃፍ ነው።

የ 33 ዓመቷ ጎልማሳ - ሕይወት የፁሁፍ መንፈሱን ያገኘሁት ከአባቴ ነው ትላለች። ፌስ ቡክ ላይ ብዙ አንባቢዎች አሏት። « ነቆራ እና ሌሎችም ወጎች ከሕይወት እምሻው ጋር» ይላል የሕይወት እምሻው የፌስ ቡክ ገፅ፤ ከ 71 600 በላይ ሰዎች ገጿን ወደውላታል።

በርካቶችም ከታሪኩ በታች አስተያየታቸውን ይገልፃሉ። ነገር ግን ሕይወት አንባቢዎቿን እጅጉን ያስደሰታቸው ታሪክ ይህ ነው ለማለት ያስቸግራል ትላለች።

ሕይወት እስካሁን የፃፈቻቸውን ታሪኮች በቁጥር አታውቃቸውም። ነገር ግን ረዝም የሚሉት እስከ 500 ይደርሳሉ ትላለች።

ሕይወት እምሻው እና በትርፍ ሰዓቷ የምትፅፋቸው አጫጭር ታሪኮች ጥቂቱን ከዚህ በታች በድምፅ ያገኙታል።

ልደት አበበ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic