«ሕወሓት ከአዲስ አበባ ሌላ ጉዳይ የለውም» ጌታቸው ረዳ | ኢትዮጵያ | DW | 08.11.2021
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

«ሕወሓት ከአዲስ አበባ ሌላ ጉዳይ የለውም» ጌታቸው ረዳ

በትግራይ ክልል ላይ የተጣሉ ዕቀባዎች ከተነሱ እና  የተቋረጡ አገልግሎቶች ከተመለሱ ሕወሓት የተኩስ አቁም ለማድረግ እና ለመደራደር ፍቃደኛ መሆኑን የግንባሩ  ቃል አቃባይ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ ። ቃል አቃባዩ ዛሬ ከዶይቼ ቬለ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ «ሕወሓት ከአዲስ አበባ ሌላ ጉዳይ የለውም» ብለዋል።

የሕዝባዊ ወያነ አርነት ትግራይ ሕወሓት ቃል አቃባይ ጌታቸው ረዳ ሙሉ ቃለ ምልልስ

በትግራይ ክልል ላይ የተጣሉ ዕቀባዎች ከተነሱ እና  የተቋረጡ አገልግሎቶች ከተመለሱ ሕወሓት የተኩስ አቁም ለማድረግ እና ለመደራደር ፍቃደኛ መሆኑን የግንባሩ  ቃል አቃባይ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ ። ቃል አቃባዩ ዛሬ ከዶይቼ ቬለ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ «ሕወሓት ከአዲስ አበባ ሌላ ጉዳይ የለውም» ብለዋል።
በአፍሪቃ ቀንድ የአፍሪቃ ሕብረት ልዩ ልዑክ ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆ ከሕወሓት ሊቀመንበር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ጋር ተገናኝተው መነጋገራቸውን ያነሱት አቶ ጌታቸው ፤ የንግግሩ ይዘት  በሂደት ያለ በመሆኑ ዝርዝር ጉዳዮችን ከመግለጽ ተቆጥበዋል። 
የሕወሃት ቃል አቃባይ ጌታቸው ረዳ ድርጅታቸዉ ይፈፅማቸዋል ስለተባሉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ ከሕዝብ ስለሚደርስበት ተቃዉሞ፣ ከዩናይትድ ስቴትስ ይሰጠዋል ስለሚባለዉ ድጋፍ፣ ከሌሎች ስምንት ቡድናት ጋር ስለመሰረተዉ ትብብር እና በተያያዥ ጉዳዮች ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች መልስ ሰጥተዋል።
 ነጋሽ መሐመድ አነጋግሯቸዋል። 
 
Audios and videos on the topic