ሕወሃት/ኢሕአዴግ ስልጣን የያዘበት 26ኛ ዓመት | ኢትዮጵያ | DW | 28.05.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ሕወሃት/ኢሕአዴግ ስልጣን የያዘበት 26ኛ ዓመት

የደርግ አገዛዝ የተወገደበትን ዕለት የሚያስታውሰው ግንቦት 20 በመላው ሀገሪቱ በመከበር ላይ እንዳለ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ። ዘገቦቹ መሠረት የዘንድሮው መሪ ቃል "የሕዝቦችን እኩልነትና ፍትሐዊ ተጠቃሚነት ያረጋገጠ ፌደራላዊ ስርዓት እየገነባች ያለች ሀገር-ኢትዮጵያ" የሚል ነው።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 06:07

የግንቦት 20 አከባበርና የተቃዋሚ አስተያየት

የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ እና ከጥቂት ቀናት በፊት የዓለም ጤና ድርጅት ዳሬክተር ሆነው የተመረጡት ዶክተር ቴዎድሮስ አድኃኖም አዲስ አበባ ላይ በተዘጋጀው ሥነ- ስርዓት ላይ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል። በአዲስ አበባ ስለነበረዉ የግንቦት 20 አከባበር የአዲስ አበባዉ ወኪላችንን በስልክ አነጋግረነዉም ነበር። በሌሎች አካባቢዎች ዕለቱ እንዴት እየተከበረ እንደሚገኝ የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ  በአጭሩ ብአዴን የከተሞች የፖለቲካ መምርያ ኃላፊ አቶ ደሳለኝ አስራደ  ለዶይቸ ቬለ ገልጸዋል። በሌላ በኩል የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት - መኢአድ ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ በዛብዝ ደምሴ  ግንቦት 20ን በማስመልከት  «መንግሥት አድርጌያለሁ ብሎ የሰነዘራቸው የዲሞክራሲና ሌሎች መብቶችን በአፍ ብቻ እንጂ በተግባር እያየናቸው አይደለም» ብለዋል።  

ዮሃንስ ግብረግዚአብሄር  

አዜብ ታደሰ

 

 

Audios and videos on the topic