ሕብረተሰብና አዲሲቷ አፍሪቃ | በማ ድመጥ መማር | DW | 22.10.2008
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

በማ ድመጥ መማር

ሕብረተሰብና አዲሲቷ አፍሪቃ

በማዳመጥ መማር የተሰኘው ዝግጅት አፍሪቃ ውስጥ ሕዝብ ሊኖረው ስለሚችል ሚና ለምን ትኩረት እንደሚያደርግ የተለያዩ ምክንያቶችን ይነቅሳል።

default

ስልጣን ለሕዝብ

በጣም ብዙ አፍሪቃውያን የተሻለች አፍሪቃን በመፍጠር ሂደት ቀጥተኛ ተሳትፎ በማድረግ ላይ ይገኛሉ። ሕዝቧ፤ ዴሞክራሲ የሰፈነባት፣ ከሙ ስና የፀዳችና ብሔራዊ ዕርቅ የምታስተናግድ አህጉርን ይሻል። የአህጉሪቱን ገፅታ ሊቀይር የሚችል፤ ንቁና ነገሮችን ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚ ያይ ማ ኅበረሰብ እየተፈጠረ ነው።

በዛምቢያ ፍሬደሪክ ቺሉባ እንደአውሮጳውያን አቆጣጠር በ2002ዓ.ም ፕሬዝደንቱን ለ3ኛ ጊዜ አንዳይወዳደሩ የሚ ያግደዉን አንቀጽ ከህገ-መንግስቱ እንዲሰረዝ ሐሳብ አቀረቡ። መንገዱ ቀላል እንደሚሆንም ገምተው ነበር። የሕዝብ ተቃውሞ ግን የፓርላማ አባላቱ የፕሬዝደንቱን ሐሳብ ከማስፈፀም እንዲቆጠቡ ነዉ ያደረጋቸው።

ጎህ ሲቀድ

በብዙ የአፍሪቃ ሃገሮች የሙ ሰኞችና አምባገነን ፖለቲከኞች ጀምበር እየጠለቀች ነው። የተለያዩ ችግሮች ቢኖሩም ሕዝቦች ከመሪዎቻቸው ብዙ እየጠበቁ ነው። መንግስታዊ ባልሆኑ አገር በቀል የስቪክ ማህበራት እየታገዙ ዲሞክራሲያዊና ተጠያቂነት ያላቸው ፖለቲከኞች በመንግስት መዋቅር ውስጥ እንዲኖሩ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው እያሰሙ ይገኛሉ።

ስልጣን ለሕዝብ

በማዳመጥ መማር የተሰኘው ዝግጅት አፍሪቃ ውስጥ ሕዝብ ሊኖረው ስለሚችል ሚና ለምን ትኩረት እንደሚያደርግ የተለያዩ ምክንያቶችን ይነቅሳል።ዝግጅቶቹ በፖለቲካ ብቻ ሳይወሰኑ አፍሪቃ ውስጥ ያሉ ስቪክ ማ ኅበራት ድህነትን ከማስወገድና ብሔራዊ ዕርቅን ከመፍጠር አንፃር ሊኖራቸው ስለሚችል ሚና ይመረምራሉ። በማዳመጥ መማር አድማጮቹን፤ ከላይቤርያ አስከ ኬንያ ያሉ ዜጎች አዲሲቷን አፍሪቃ ለመፍጠር ስለሚያደርጉት ትግል ለማሳየት በምናብ ይዟቸው ይጓዛል።

በማዳመጥ መማር የተሰኘው ዝግጅት በስድስት ቋንቋዎች ይቀርባል። ቋንቋዎቹም አማርኛ፣ ኪስዋሂሊ፣ ሃውሳ፣ ፈረንሳይኛ፣ እንግሊዝኛና ፖርቱጋልኛ ናቸው። ተጨማሪ መረጃ ወይም ዝግጅቶቹን ለማዳመጥ ከፈለጉ እባክዎን www.dw-world.de/learning-by-ear የተሰኘውን ድረ ገጻችንን ይጎብኙ።በማዳመጥ መማር የተሰኘው ፕሮጀክት በጀርመን ፌደራላዊ የውጪ ጉዳይ ሚ ኒስቴር ይታገዛል።