ሔይቲን የመታዉ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋና ርዳታዉ | ዓለም | DW | 14.01.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

ሔይቲን የመታዉ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋና ርዳታዉ

ትናንት ሔይቲን የመታዉ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ በመቶ ሺሕ የሚቆጠር ሕዝብ ሳይፈጅ እንዳልቀረ እየተነገረ ነዉ።በሬክተር መመዘኛ ሰባት የተለካዉ የመሬት መንቀጥቀጥ በአካባቢዉ የሁለት መቶ አመት ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ከፍተኛ ነዉ።

default

በተለይ ርዕሠ-ከተማይቱ ፖርት ኦ ፕረስን ክፉኛ ያርገፈገፈዉ አደጋ ከሐገሬዉ ሕዝብ በተጨማሪ አለም አቀፍ ሠላም አስከባሪ ወታደሮችን፥ የርዳታ ድርጅት ሠራተኞችን ገድሏል፥ አቁስሏልም።በአደጋዉ የተጎዳዉን የደሐይቱን ሐገር ሕዝብ ለመርዳት መንግሥታትና አለም አቀፍ ድርጅቶች ወታደሮች፥ የአደጋ ሠራተኞች፣ ሐኪሞችና መሳሪያዎች እያዘመቱ ነዉ።የገንዘብና የቁሳቁስ ርዳታም እየላኩ ነዉ።የዋሽንግተኑ ወኪላችን አበበ ፈለቀ ተጨማሪ ዘገባ ልኮልናል።

አበበ ፈለቀ /ነጋሽ መሀመድ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic