ሐሳብን የመግለጽ መብትና ፀረ-ሽብር ሕጉ | ኢትዮጵያ | DW | 25.10.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ሐሳብን የመግለጽ መብትና ፀረ-ሽብር ሕጉ

ዞን ዘጠኝ በመባል የሚታወቁትና በእነ ሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ ቀርቦባቸው ለአንድ ዓመት ከስድስት ወር በእስር ላይ የነበሩት ድረ-ገጽ ፀሐፍት እና ጋዜጠኞች ክሱ ተነስቶላቸዋል።

ሐሳብን የመግለጽ መብትና ፀረ-ሽብር ሕጉ

ድረ- ገፅ ተጠቅመው የተለያዩ ጽሑፎችን በማውጣት ሕገ- መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድ ተንቀሳቅሰዋል በሚል ከተከሰሱት ድረ-ገፅ ጸሓፍት መካከል አምስቱ ታሳሪዎች ባለፈዉ ዓመት መጨረሻ ሐምሌ የልዕለ ኃያልዋ አገር የዩኤስ አሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ኢትዮጵያን ለመጎብኘት ሳምንት ሲቀራቸዉ ነበር በድንገት ከእስር የተለቀቁት። ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ አርብ ደግሞ በሌለችበት የተከሰሰችዉ ወጣት የድረ-ገጽ ጸሐፍትን ጨምሮ ሌሎች አራት ተከሳሾች መከላከል ሳያስፈልጋቸው ነበር ክሳቸዉ የተነሳዉ።

ባለፈዉ ረቡዕ ያስቻለዉ የፊደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በእስር ላይ የነበረዉን የመጨረሻዉን የዞን ዘጠኝ ድረ -ገጽ ጸሐፊ በ20 ሺህ ብር ዋስ ከእስር ቤት ወጥቶ እንዲከላከል ወስኗል። የጋዜጠኞች መብት ተቆርቋሪ ድርጅት CPJ፤ የ2015 ዓለማቀፍን የፕሬስ ነጻነት ተሸላሚ ያደረጋቸዉ ወጣት ጸሐፍትና ጋዜጠኞች ከእስር እንዲፈቱ ጥሪ ሲያስተላልፍ መቆየቱ ይታወሳል። ሐሳብን በነፃ የመግለፅ መብት፤ ፀረ ሽብር ሕጉ አተገባበር የመወያያ ርዕሳችን ነዉ።

የውይይቱ ተሳታፊዎች አቶ ጌታቸዉ ረዳ የኢትዮጵያ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር፤ ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያም የዓለም አቀፍ ሕግ ባለሞያ፤ አቶ ተማም አባቡልጎ ጠበቃ፤ እንዲሁም ጋዜጠኛ ፋሲል ግርማ ናቸዉ። ሙሉ ዉይይቱን የድምፅ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ። አስተያየቶን በፌስ ቡክ ገፃችን ላይ ያኑሩ።

አዜብ ታደሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

Audios and videos on the topic