ሐረር ከተማና መስህቦችዋ | የባህል መድረክ | DW | 25.01.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

የባህል መድረክ

ሐረር ከተማና መስህቦችዋ

በኢትዮጵያ ጅብ ተከብሮ ስጋ ጎርሶ፤ ገንፎ ተገንፍቶ ቀርቦለት የሚኖረዉ ሐረር ከተማ ላይ ነዉ። ከጥር ስምንት እስከ 10 የሐረሬ ጅቦችና የከተማዋ ነዋሪዎች አንድ ላይ የሚያከብሩት የአሹራ በዓል ይሰኛል። ሐረሪዎች የሚያከብሩት ሶስት በዓላቶች መካከል ለጅብ ገንፎ የማብላት ስነ-ስርዐት አንዱ ነዉ።

በምስራቅ ኢትዮጵያ ከአዲስ አበባ 525 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘዉ ሐረር ከተማ አምስት በሮች ባሉትና ጀጎል ተብሎ በሚጠራዉ ዝነኛ ግንብ የተከበበች ስትሆን፤ በሰባተኛዉ እና ዘጠነኛዉ ክፍለ ዘመን መቆርቆርዋን፤በከተማዋ የሚገኙ ታሪክ አዋቂዎች ይናገራሉ። የዕለቱ የባህል ቅንብራችን የሐረር ከተማን ያስቃኘናል። ከምስራቅ አፍሪቃ ጥንታዊ ከተሞች አንዷ በመሆን በተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት UNESCO በቅርስነት የተመዘገበችዉ ሐረር ከተማ 4ኛዉ የስልምና ሃይማኖት ቅዱስ ከተማ ተብላም ትጠራለች። የሐረሪ ህዝብ ክልላዊ መንግሥት የባህል ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ተጠሪ አቶ አዩብ አብዱላሂ ስለ ሐረር ከተማ ጥንታዊነት እንዲህ ያስረዳሉ። የጀጎል ግንብ ማለት ሐረሪ ዎች መኖርያ ማለት ነዉ ሲሉም ገልፀዉልናል። ሙሉዉን ቅንብር የድምፅ ማድመጫዉን በመጫን ያድምጡ!

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሀመድ

Audios and videos on the topic