ሌጎሰ-አፍሪቃዊቷ ግዙፍ ከተማ | ይዘት | DW | 23.09.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ይዘት

ሌጎሰ-አፍሪቃዊቷ ግዙፍ ከተማ

«እኔ ሐገር አንዲት ሴት ስታስነጥስ የሰማ «ሴታሴት» ይላታል።የቃሉን መዕልክት ተረድቼዉ አላዉቅም።ግን እንዲያዉ በየዕለቱ- የሚሰማኝን በትክክል የሚገልፅ ቃልስ አለ ይሆን?

default

ሌጎሰ-መጓጓዢያ

ስዕሎች
«ደሕና ጊዜ ይመጣል» ብላዋለች-ሴፊ አታ የመጀመሪያ ሥራዋን።ሌጎስ የሚኖሩ የሁለት ሴት ወጣቶች ሕይወትን ይቃኛል።መፅሐፉ።አኒታን እና ሼሪ ጓደኞች ናቸዉ።ሁለቱም ከሌጎስዋ ጥዱ መንደር ኢኮዪ ይኖራሉ።ኢኮይ-የመኪና ኩርኩርታ-ጥሩምባ፥ የሰዎች ሁካታ-ጫጫታ ኩርኩርታና-ትርምስ ብዙም አይታይ-አይሰማባትም።አኒታን ክርቲያን ናት።አዱኛ የሰገደችላቸዉ ቱጃር አባቷ እዉቅ ጠበቃ ነበሩ።የናይጀሪያ በወታደራዊ አምባገነኖች ትገዛ በነበረበት ወቅት ለሰብአዊ መብት መከበር ሲከራከሩ ነበር።

ለቀቅ ካለ ቤተሰብ ተወልዳ ያደገችዉ ሼሪ ሙስሊም ነች።አንድ ከፍተኛ የጦር መኮንን አስቀምቷታል። መኮንኑ ከቤት-እንድትወጣ ብዙ አይፈቅድላትም።የሁሉቱ ወጣቶች ምኞት ሙከራ ወንዶች በሚጫኑት ዓለም -ዓለማቸዉን ማግኘት እና እንዳቀሙ መከላከል ነዉ።

«እኔ ሐገር አንዲት ሴት ስታስነጥስ የሰማ «ሴታሴት» ይላታል።የቃሉን መዕልክት ተረድቼዉ አላዉቅም።ግን እንዲያዉ በየዕለቱ- የሚሰማኝን በትክክል የሚገልፅ ቃልስ አለ ይሆን? እና ለዚሕስ ብሔል ቃል ማግኘትስ አስፈላጊ ነዉ?የሴቶችን ምፀት አስተዉያለሁ።በእድገት ሒደታቸዉ ጠንካራና ዝምተኛ፥ ደግና ለስላሳ እና ደግሞ ስሜታዊ ተብለዉ በሰወስት የሚከፈሉ ግን የሚሊዮን ሰዎች አይነት ስብዕና አላቸዉ።ከዚሕ በተረፈ ያሉት ሴቶች በሙሉ አስቸጋሪ የሚባሉ ናቸዉ»

Blick über Lagos Nigeria

አዲስና አረጌ

የዚሕ ታሪክ መቼት (ጎርጎሮሳዉያኑ አቆጣጠር) በ1960ዎቹ፤በ70ዎቹና በ 80ዎቹ አመታት በነበረዉ የሌጎስ ገፅታ ላይ የሚያጠነጥን ነዉ።ያኔ ሌጎስ የናይጄሪያ ርዕሠ-ከተማ ነበረች።በዚያ ዘመን፣ ናይጄሪያ 1960ዎቹ ነፃ ስትወጣ ያፈራቻቸዉ የመንግሥት ባለሥልጣናት እና የሌሎች ልሒቃን ቤተሰቦች የኢኮዪ ዉስጥ ይኖሩ ነበር።ሴፊ አታ ራስዋ በ1964 የነበረዉን አለም ብርሐን ቃኝታዋለች።ወደ ቪክቶሪያ ደሴት በሚወስደዉ አዉራ ጎዳና ላይ ባለ አራት-መንገዱ ድልድይ ሲገነባ የነበረዉ ሁኔታ ትጠቅሳለች።

«በጣም አስደሳች ነበር።ወዳጆቼን ለመጎብኘት አንዳዴ በእግሬ፥ አንዳዴ ደግሞ በብስኬሌት እጓዝ ነበር።---ዛሬ ቢሆን ኖሮ በጣም አደገኛ በሆነ ነበር።እኔ ያኔ ያደረኩትን ልጆቼ ዛሬ እንዲያደርጉት በጭራሽ አልፈቅድላቸዉም።»

MC Lagos Friseurin

ፀጉር ሥራ

ሐብታሞቹ ይገነባሉ።
ያሁኖቹ የኢኮዪ ነዋሪዎች በብስክሌት መጓዝን በፍፁም ሊያስቡት አይችሉም።እንደ «ፎር ሹር ኢስቴት» መንደር ብዙዎቹ በትላልቅ የግንብ አጥሮችና በመቆጣጠሪያ ኬሌዎች ተቃርጠዉ ነዉ የሚኖሩት።በተለያየ ቀለም ያሸበረቁት ትላልቅ ሕንፃዎች ተገጥጥጠዉበታል።እያንዳዱ ቦታ እሾሐማ ሽቦ በተጠመጠመበት ትላልቅ የግብ የታጠረ ነዉ።

ሴፊ አታ እንደምገልፀዉ የመካከለኛዉ መደብ የሕብረተሰብ ክፍል እዚሕ መንደር መኖር ሲበዛ ነዉ-የሚከብደዉ።---

ነጋሽ መሐመድ

DW.COM