ሊቢያ እና የመንግስታቱ የጦር እርምጃ | ዓለም | DW | 20.03.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

ሊቢያ እና የመንግስታቱ የጦር እርምጃ

የምዕራባዉያን መንግስታት እና የአረብ ሊጋዉ ትናንት ፓሪስ ላይ የሞአመር ጋዳፊን ሃይል ለማምከን ከተስማ በኳላ ከትናንት ምሽት ጀምሮ በተለይ የፈረንሳይ የእንግሊዝ እና የዪናይትስ ስቴትስ የጦር ሃይሎች የኮነሪል ጋዳፊን ቁልፍ የጦር ሰፈሮች እየደበደቡ ነዉ።

default

ጀርመን በወታደራዊዉ እንቅስቃሴ ባትሰለፍም የጋዳፊን ጭፍጨፋ በጽኑ በመቃወም ጋዳፊ ስልጣናቸዉን ለሊቢያ ህዝብ እንዲያስረክቡ ጠይቃለች።

በመካከለኛዉ ምስራቅ እና በሰሜናዊዉ ምስራቅ አካባቢ ህዝባዊ እንቅስቃሴ ከጀመረ ሰባት ሳምንት ግድም ሆነዉ። በቱኒዝያ ቤን አሊን ካስወገደ በኳላ፣ በግብጽ ሙባረክን አባሮ፣ ግብጽ የህገ መንግስት ማሻሻያ ለዉጥ ለማድረግ ህዝበ ዉሳኔ ስታደርግ ዉላለች። በየመንም ፕሪዘንት አሊ-ሞሐመድ-ሣሌህን ከሥልጣን ለማባረር ህዝቡ ሰላማዊ ሰልፍ እየወጣ ከመንግስት በኩል የሚወርድበትን ዱላና ግድያ መቃቃም አቅቶታል። ለአርባ ሁለት አመት የሊቢያን ምድር በአንባገነን መሪነት የተቆጣጥርዋት ኮነሪል ሞአመር ጋዳፊም የገዛ ህዝባቸዉን በሮኬት እየደበደቡ አልቃይዳን እየተዋጋሁ ነዉ ይላሉ። ይህን መመልከት እና መስማት የተሳነዉ የመንግስታቱ ድርጅት እና የአረቡ አለም ጋዳፊ በህዝብ ላይ የሚያደርሱት ጭፍጨፋ ይቁም ብሎ አፈሙዙን ወደ ጋዳፊ ማነጣተሩን ጀምሮአል። ትናንት ቀትር ላይ ምዕራባዉያን መንግስታት እና የአረብ ሊጋ የሊቢያዉ መሪ ኮነሪል ሞአመር ጋዳፊ ላይ ወታደራዊ እርምጃ ለመጀመር ፓሪስ ላይ በዉይይት ካጸደቁ በዓላ አመሻሹ ላይ ሊቢያ ሞአመር ጋዳፊ የጦር ሰፈር ላይ የጥቃት ሮኬታቸዉን ማዥጎድጎድ ጀመሩ። አበር መንግስታቱ ጋዳፊ በገዛ ዜጎቻቸዉ ላይ የጀመሩትን ድብደባ እንዲገቱ በወታደራዊ እርምጃ በሊቢያ ለመጀመር በፈረንሳይ መሪነት ፓሪስ ላይ በዉይይት ላይ ሳሉ ከቀትር በኳላ የፈረንሳይ የጦር አሮፕላኖች በሊቢያ ላይ ማንዣበባቸዉን ጀምረዉ ነበር። ብዙም አልቆየ የመንግስታቱ መሪዎች ወታደራዊ እርምጃ እንዲጀመር ካጸደቁ በኳላ የፈረንሳይ አዉሮፕላኖች በጋዳፊ ወታደሮች እና የጦር ሰፈር ጥቃት ጀመሩ። አበር መንግስታቱ ፓሪስ ላይ ተሰብስበዉ ዉሳኔያቸዉን ካስተላለፉ ከጥቂት ደቂቃ በኳላ የፈረንሳዩ ፕሪዝደንት ኒኮላ ሳርኮዚ ባሰሙት ንግግር «የጦር አዉሮፕሎናቻችን በቤንጋዚ ላይ በህዝባዊ አማጽያን ላይ የሚደርሰዉን ጥቃት ይከላከላሉ። ሌሎች አዉሮፕላኖቻችንም በሌሎች አካባቢዎች የሲቪሉን ማህበረሰብ ይጠብቃሉ» በዚህም ሳርኮዚ የጋዳፊን የግፍ ጭፍጨፋ በማድረስ ላይ መሆናቸዉን በግልጽ በማስጠበቅ በሊቢያ ወታደራዊ እርምጃ እንዲካሄድ በፓሪስ ላይ ፊርማቸዉን ላስቀመጡት በሙሉ የተረጋገጠ መልስን አስቀጡ። በፓሪሱ ጥምር ጉባኤ ላይ የአረብ ሊጋዉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሊቀመንበር ባን ኪሙን የአሜሪካንዋ ጠቅላይ ሚኒስትር ሄላሪ ክሊንተን እና በርካታ የአዉሮጻ አገር ተጠሪዎች ተገኝተዉበታል። የፈረንሳዩ ፕሪዝደንት በመቀጠል «ሊቢያ የወደፊት እርምጃዋን እራስዋ መወሰን ይኖርባታል። ሊቢያን ወክለን ለሊቢያ መወሰንን አንሻም። ለነጻነታቸዉ መታገላቸዉም የሊቢያዉያን ነዉ። ነገር ግን በኛ እና በአለም ህዝቦች ስም በራስ ህዝብ ላይ እንዲህ አይነት ግፍ ሲፈጸም ቁጭ ብለን ማየት አንችልም» ።

Nicolas Sarkozy Frankreich Libyen Luftangriffe


ብሪታንያ ዪናይትድ ስቴትስ እና ካናዳ በሊቢያ ወታደራዊ እርምጃ ላይ ግንባር ቀደሙን ስፋራ ይዘዉ ሲገኙ ከነዚህ መካከል የትኛዉ አገር ወታደራዊዉን እርምጃ በመሪነት ስፍራ እንደያዘ ግን በግልጽ የተቀመጠ ነገር የለም። በመሪነቱ አኳያ ብዙ ስምምምነት ያላገኘ ሃሳብም አለ። እንግሊዝ የሰሜን ጦር ቃል ኪዳን አባል አገራት ጥምር ጦርን በመምራት በሊቢያዉ ወታደራዊ እርምጃ ላይ በቀደምትነት መካፈልን ስትሻ፣ የአረብ ሊጋዉና ፈረብሳይ በበኩላቸዉ አንድ የምዕራብ አገር የጦር ጥምር በአንድ የአረብ አገር ዉስጥ በጦር መሪነት መገኘቱ ጥሩ ስሜትን እና ድጋፍን አይፈጥርም በሚለዉ ያምኑበታል። ቢሆንም ቅሉ በሊቢያ የጋዳፊን የግፍ ጭፍጨፋ ለማስቆም የጥምሩ መንግስት በሲሊያ በማልታ በቆጽሮስ የጦር ሰፈርን ዘርግቶአል። በሌላ በኩል አሁንም ቢሆን ጀርመን በሊቢያ በምንም አይነት ወታደራዊ እንቅስቃሴ ላይ ላለመሳተፍ ባሳለፈችዉ ዉሳኔ ጸንታለች። ያም ቢሆን መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ትናንት ቀትር ላይ በሊቢያ ወታደራዊ እርምጃ ለመጀመር ዉሳኔ ለማሳለፈ ፓሪስ ላይ ምዕራባዉያን መንግስታት እና የአረብ ሊጋዉ ስብሰባ ላይ በመገኘት አንድነታቸዉን አሳይተዋል። «የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ቁርጠኛ ዉሳኔን ለመከፋፈል ማንም አይሳካለትም። እኛም ከሊቢያዉን ባህበረሰብ ጉን በመሰለፍ ጋዳፊ የራሳቸዉን ህዝብ መጨፍጨፋቸዉን እንዲያቆሙ እና ጦርነቱ እንዲያበቃ እንፈልጋለን» ጀርመን በሊቢያ ላይ የጣለችዉ የነዳጅ ዘይት እገዳዋን ይበልጥ አጥብቃለች። ያ ማለት ደግሞ ጀርመን እስካሁም ከሊቢያ ያስገባችዉን የድፍድፍ ዘይት ገንዘብ ሂሳብ ለወቅቱ የሊቢያ መንግስት አትከፍልም። በአሁኑ ሰአትም ምንም አይነት የነዳጅ ዘይት ከሊቢያ አታስገባም። በሌላ በኩል ግን ሜርክል ወታደራዊ እርዳታ እንደሚያቀርቡ እንዲህ ነዉ የገለጹት «የየሰሜን አትላንቲኩን ወታደራዊ ድርጅት ኔቶ በተለይ አፍጋኒስታን ዉስጥ ተጨማሪ ሃላፊነት በመዉሰድ አዋካስ ማለት የስለላ አዉሮፕላኖቻችን ተግባር ስራዉን ለማቅለል ዝግጁ ነዉ። ሌላዉ አሜሪካዉያን በጀርመን አገር ዉስጥ ያላቸዉን የጦር ሰፈር ለጦር እንቅስቃሴ እንዲጠቀሙ እንፈቅዳለን»
በአሁኑ ወቅት በደቡብ አሜሪካ ጉብኝት ላይ የሚገኘት ፕሪዝደንት ባራክ ኦባማ በሊቢያ ወታደራዊ እርምጃ እንዲደረግ ዉሳኔ ለመድረስ ቀላል ሁኔታን እንዳልፈጠረላቸዉ ገልጸዋል። ዪናይትድ ስቴእስ በሊቢያ የበረራ እገዳ ለመጣል ዉሳኔ ለመድረስ በርካታ ግዜ ፈጅቶባቸዋል። ይህም ፕሪዝደንት ኦባማ ከሌላ ሶስተኛ ሙስሊም አገር ጋር ጦርነት ማካሄድን አለመፈለጋቸዉ ነዉ። ከኢራቅ እና ከአፍጋኒስታን በመቀጠል፣ በሌላ በኩል ኦባማ የፕሪዝደንትነትን ስልጣን እንደያዙ የመጀመርያዎቹ ሁለት አመታት ከአረብ አገራት ጋር ያላቸዉን ግንኙነት ለማሻሻል ሞክራቸዉ አይዘነጋም።
ግን በሊቢያ ሰሞኑን የጋዳፊ ተቃዋሞዎች የያዙትን ክልል በጋዳፊ ወታደሮች እየተነጠቁ በርካታ የሲቪል ማህበረሰብ እየተገደሉ እና ስቃይ ላይ እየወደቁ መምጣታቸዉ አሜሪካ ዉሳኔዉን እንድትቀበል ሆንዋል። እንደ አሜሪካዉያን አስተያየት እ.አ 1994 አ.ም አስከፊ ገጽታ የነበረዉ የሩዋንዳዉ የህዝብ ጭፍጨፋ እንዲሁም በባልካኑ ማለት በይጎዝላቭያዉ ጦርነት በግዜዉ ፈጣን እርምጃ ባለመደረጉ የብዙ ህዝቦች እልቂት ደርሶአል። »

Präsident Nicolas Sarkozy Kanzlerin Angela Merkel Libyen-Sondergipfel Elysee-Palast Paris Uno-Einsatz gegen Libyenይህንኑ ሁኔታ በትናንትናዉ እለት የዪናይትድ ስቴትሱ ፕሪዝደንት ባራክ ኦባማ በድጋሚ በማንሳት በሊቢያ ወታደራዊ እርምጃ እንዲደረግ ዉሳኔ መድረሳቸዉን እንዲህ ነበር የገለጹት «የአንድ አንባገነን መሪ በጦር ሃይሉ በጭካኔ ንጹሃንን ህዝብ ሲያጠፋ ዝም ብለን ማየት አንችልም። ይህ ግፍ በተለይ በሚስራታ እና ቤንጋዚ ከተሞች ላይ አይሎ ንጹሃን ወንዶች እና ሴቶችን በግፍ በገዛ መንግስታቸዉ ሲገደሉ አይተናል» አስራ አምስት አባል አገራትን ያቀፈዉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥዉ ምክር ቤት ባለፈዉ ሃሙስ ምሽት የበረራ ዉሳኔዉ ሲያጸድቅ አምስት አገራት ማለት ሩስያ ቻይና ህንድ ጀርመን ብራዚል በሊቢያ የበረራ እገዳ ዉሳኔን በድምጸ ታቅቦ አልፈዋል። ይህን የሰሙት የሊቢያዉ ፕሪዝደንት ኮነሪል ሞአመር ጋዳፊ የፈረንሳዪን ፕሪዝደንት ሳርኮዚን ጓደኛዪ ብንሆንም ሳያመዉ አይቀርም ሲሉ የነዳጅ ዘይት ማምረቻ ሚኒስትራቸዉ ደግሞ በሊቢያ በስራ ላይ የነበሩ የነዳጅ ድርጅት ኩባንያዎች ወደ ሊቢያ ተመልሰዉ ስራቸዉ እንዲቀጥሉ ካለበለዝያ ግን ኮንትራቱን ለህንድ እና ለቻይና እንደሚሰጡ ገልጸዋል። ቻይና ትናንት ማታ በሊቢያ ላይ የተጀመረዉን ወታደራዊ እርምጃ ስትነቅፍ ሩስያ የጥምር መንግስታቱ ከጀመረዉ አየር ጥቃት ራቅ በማለት የሊቢያን መንግስት ከአአማቀፉ ማህበረሰብ ጋር ድርድር እንዲያደርግ ጥሪዋን አሳልፋለች።

Infografik militärisches Drohpotential Libyen II


በእንግሊዝ ፈረንሳይ እና ዪናይትድ ስቴትስ የሚመራዉ የጥምር መንግስታቱ በሊቢያ ዘመቻ ትናንት ምሽት ብቻ ከሜዲተራንያን ባህር ከሚገኙት የጦር መርከቦች ወደ በሊቢያ እጋዳፊ የጦር ሰፈር ላይ መቶ ያህል ሮኬቶችን አዝንቦአል። ከጥቁ በኳላ የሊቢያዉ ፕሪዝደንት ኮነሪል ሞአመር ጋዳፊ በራድዮ ባሰሙት ጥሪ የጦር መሳርያ ማከማቻ ለሊቢያዉያን ክፍቼ የሜዲተራንያንን አካባቢ የደም መፋሰሻ አደርገዋለሁ ሲሉ መዛታቸዉም ተሰምቶአል። በሊቢያ የጋዳፊን ጦር ለመምታት የሚደረገዉ ትግል በዛሪዉ እለትም ቀጥሎ ቢያንስ አስራ ስምንት ያህል የዪናይድ ስቴትስ የጦር አዉሮፕላኖች በሊቢያ የጋዳፊን ቁልፍ ቦታዎችን ማጥቃቸዉን አፍሪኮም የተሰኘዉ የአፍሪካ አሜሪካ የጦር ትብብር ድርጅት ቃል አቀባይ መግለጹ ተነግሮአል። የፈረንሳዪም የጦር አዉሮፕላኖች ጥቃታቸዉን በመቀጠል የጋዳፊን የጦር ተሽከርካሪዎች ማዉደማቸዉ ተያይዞ ተጠቅሶአል። በሌላ በኩል የጋዳፊ የጦር ሃይሎችም በበኩላቸዉ ሚስራታ ከተማ ላይ ከፍተኛ ጥቃት ማድረሳቸዉን የአይን ምስካሪን ገልጾ የደረሰ ዘገባ ያሳያል።
በሊቢያ ሞአመር ጋዳፊ ላይ የሚደረገዉ ዘመቻ ትናንት አመሻሹ ላይ ከጀመረ ወዲህ ስንት ሰዎች በጥቃቱ እንዳለፉ የተረጋገጠ መግለጫ ባይኖርም በቦታዉ የሚገኙ ጋዜጠኞች እንደዘገቦት አስራ አራት ሰዎች ሞተዋል። የዪናይትድ ስቴትሱ የጦር መምርያ አዛዥ በበኩላቸዉ በሊቢያ የነበረዉ የጦር ስምሪት አመርቂ ነበር ብለዋል።
የመንግስታቱ ጥምር ጦር በሊቢያ የጋዳፊን ቁልፍ የጦር ቦታዎች ላይ ጥቃት ከጀመረ በኳላ የሊቢያ መንግስት የቴሌቭዥን ጣብያ አርባ ስምንት ያህል ሰዎች መገደላቸዉን ገልጾአል። ከሌላ ወገን የተረጋገጠ ማስረጃ ባይኖርም። አለም አቀፉ የቀይ መስቀል ድርጅትም በበኩሉ የሲቪል ማህበረሰቡን ደህንነት ሁኔታ መዘንጋት እንደሌለበት እና በሲቢል እና በወታደራዊ እንቅስቃሴ መካከል ያለዉ ልዪነት እንዳይዘነጋ ጥሪዉን አቅርቦአል።

አዜብ ታደሰ
መስፍን መኮንን