ለ2011 የተሸጋገረው የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ምርጫ ጉዳይ   | ኢትዮጵያ | DW | 08.03.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ለ2011 የተሸጋገረው የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ምርጫ ጉዳይ  

አንድ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ምርጫው ከሀገራዊው ምርጫ ጋር ቢካሄድ እንደሚሻል ተናግረዋል። ሌላው ደግሞ በዚህ ዓመት መካሄዱን መርጠዋል። ሦስተኛው አስተያየት ሰጭ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ለተፈናቀሉ ዜጎች መፍትሄ ሳይገኝ የነዚህ ሁለት ከተሞች ምርጫ ብቻ ሳይሆን ሀገራዊውንም ምርጫ ማካሄድ አይገባም ብለዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:00

የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ምርጫ ጉዳይ

የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባለፈው ዓመት የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋን ምርጫ ለዘንድሮ አስተላልፎ ነበር። ይሁን እና ዓመቱ ቢጋመስም በ2011 ይካሄዳል ስለተባለው የሁለቱ ከተሞች ምርጫ ከምርጫ ቦርድ በኩል የተሰማ ነገር የለም ይላል የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር። ዮሐንስ በጉዳዩ ላይ ካነጋገራቸው የተቃዋሚ ፓርቲዎች መሪዎች አንዱ ምርጫው ከሀገራዊው ምርጫ ጋር ቢካሄድ እንደሚሻል ተናግረዋል። ሌላው ደግሞ በዚህ ዓመት መካሄዱን መርጠዋል። ሦስተኛው አስተያየት ሰጭ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ለተፈናቀሉ ዜጎች መፍትሄ ሳይገኝ የነዚህ ሁለት ከተሞች ምርጫ ብቻ ሳይሆን ሀገራዊውንም ምርጫ ማካሄድ አይገባም ብለዋል። ስለ ጉዳዩ የምርጫ ቦርድን አስተያየት ለማግኘት DW ያደረገው ሙከራ አልተሳካም። ዝርዝሩን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ያቀርብልናል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ኂሩት መለሰ

ተስፋለም ወልደየስ

Audios and videos on the topic