ለ13 አንጋፋ ጋዜጠኞች እና የመገናኛ ብዙሃን ባላሙያዎች እውቅና ተሰጠ
ቅዳሜ፣ ኅዳር 7 2017ታላላቆችን እናክብር በሚል በ1960ዎቹና በ1970ዎቹ አገራቸውን ያገለገሉ ቀደምት ጋዜጠኞች አንጋፋ የመገናኛ ብዙሃን ባላሙያዎች በዛሬው ዕለት ሽልማት ምስጋና ተችሯቸዋል። በዚህ መርሀ- ግብር 13 የቀድሞ ጋዜጠኞች ዕውቅና ተበርክቶላቸዋል። ተመስጋኝ ጋዜጠኞች፣ አቶ አስፋው ኢዶሳ፣ ወይዘሮ አባይነሽ ብሩ፣አቶ ሀዲስ እንግዳ፣ አቶ ዋጋዬ በቀለ፣ወይዘሮ ሚሊየን ተረፈ፣አቶ ሀይሉ ወልደፃድቅ፣አቶ ተሾመ ብርሀኑ ከማል ፣አቶ ተክሉ ታቦር፣ አቶ ይንበርበሩ ምትኬ፣ አቶ ታዬ በላቸው ፣አቶ ግርማይ ገብረፃድቅና አቶ ኢሳያስ ሆርዶፋ ናቸው።ዝግጅቱ ላይ እንደሚመሰገኑ ከተመረጡ በኃላ ህይወታቸው ያለፈው የሚድያ ሰው ሙልጌታ ወልደሚካኤልም በልጆቻቸው አማካይነት ዕውቅናው ተሰጥቷቸዋል።
ከመታሰር እስከ መባረር በግድ የፖለቲካ ፓርቲ አባል ከመሆን ስራቸው ስማቸውን እንዳይዞ እንዳይወጣ እስከመከልከል ያለጡረታ ከስራ መሰናበት እና ለቤተሰቦቻቸው ግዜ አለማግኘት ስራቸው እስከማሳገድ የደረስ ፈተና ነበረባቸው።በዚህ ሁሉ ደከመኝ ሰለቸኝ አበሳ እና ፈተና በዛብኝ ሳይሉ ሙያቸውን ወደው እና አክብረው ሀገራቸውን እና ህዝባቸውን አገልግለዋል ዕውቅና የተቸራቸው እነዚህ አንጋፋ የሚድያ ሰዎች ከዚህ ቀደም ተገቢውን ዕውቅና ሳያገኙ የቀሩና በሌሎች የሽልማት መርሀ ግብሮች ያልተካተቱ ናቸው ።
በጋዜጠኝነት እና በሚዲያ ስራ ላይ እድሜቸውን ሙሉ ሰርተው ከዚህ ቀድም ተገቤውን ምስጋና ሳያገኙ የቆዩ እና አሁን ምስጋነ የተቸራቸው 13 አንጋፋ የሚድያ ሰዎች ታሪካቸው ሲነገር ማስገረሙ እና ተሰምቶ ካለመጠገቡ ባሽገር ይህ የጋዜጠኝነት ሙያ ትላንት የነበረበት ዳፋ እና ፍዳ አሁንም ከ ዚሁ ፈተና አዙሪት አለመውጣቱ ያሳያል
በሪዲዪና በቴሌቪዥን እንወዳቸው የነበሩ ፕሮግራሞች ትጉዋዥ ካሜራችን፣ህብረትትርኢት ጤናችን እንንጋግርብት እርስዎም ይሞክሩት፣የእንግሊዝ እግርኩዋስ ጨዋታን ማታ ማታ በ ኢትዮጵያ ቴሊቨዥ ያስጀመሩ፣አለም እንዴት ስነበተች የተስኙት ፕሮግራሞች የመስረቱ፣ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ቴሌዥን ፕሮግራም ሲጀመር እንኩዋን ደስ ያላችሁ ሲሉ ለ ኢትዮጵያ ህዝብ ያበሰሩ ደራሴና ጋዜጠኛ በህይወት ያሉትንም የሌሉትንም አስታውሶ የዘከረ ነበር።
ሁኔታው ሳይመቻች መንገዱ ሳይቀና ይህንን የጋዜጠኝነት ስራ መስራት የነበረውን ትግል እና የሙያ እርካታ ለ DW የገለፁት ጋዜጠኛ አባይነሽ ብሩ አሁን በሙያው ላይ የተጋረጠው ፈተና ሁሉም ተናጋሪ ጋዜጠኛ ነው መባሉ ነው ሲሉ የሙያው ስነምግባር እና ክብር ባለሙያዎችም ፈተና ውስጥ ገብተዋል ይላሉ ።
በ 19 60፣ ና 70ዎቹ አንጋፈ የጋዜጠኞች የምስጋና ፕሮግራም መመስገንም ማመስገንም መታድል ነው ይህንን ታልቅ ሀሳብ ያሰበው ጋዜጠኛ እዝራ እጅጉ እና ተወዳጅ ሚዲያ የ ባለታሪኮችን ስራ በህትመት አዘጋጅቶ ለ ኣብርሆት መፅሀፍት ቤት መበርከቱ ተነግሮዋል።
ሙሉ ዝግጅቱን የድምፅ ማዕቀፉን ተጭነው ያድምጡ።
ሀና ደምሴ
ፀሐይ ጫኔ