ለጎዳና ተዳዳሪ ሕጻናት የተሐድሶ ማዕከል | ኢትዮጵያ | DW | 19.06.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ለጎዳና ተዳዳሪ ሕጻናት የተሐድሶ ማዕከል

የአማራ ክልል የጎዳና ተዳዳሪ ለነበሩ ሕጻናት የተሃድሶ ማዕከል ሊያሠራ ነው። ከጎዳና ተመልሰው ወደ ቤተሰቦቻቸው  የሚቀላቀሉ  ሕጻናት  ተመልሰው  ወደ  ከተማ  እንዳይመጡ  የሚያደርግ  እንደሆነ የክልሉ  ሴቶች፣ ሕጻፃናት እና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ አስታውቋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:12

«ለሕጻናቱ የተሃድሶ ማዕከል ሊያሠራ ነው»

በአማራ ክልል በተለያ ምክንያቶች ከመኖሪያ ቀያቸው ወደ ከተማ የሚገቡ ሕጻናት ቁጥር እጨመረ ነው፡፡  የአማራ ክልል ሴቶች፣ ሕጻናት እና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ የጎዳና ተዳዳሪ ሕጻናትን ከኅብረተሰቡ  ጋር  በመነጋገር  ወደመጡበት  እንደሚልክ  ቢናገርም  ወደ ከተማ  የሚፈልሱ  ሕጻናት  ቁጥር  ግን  አሁነም አልቀነሰም፡፡

ዓለምነው መኮንን ሰሞኑን  ከሰሜን ጎንደር  ዞን አካባቢ  ወደ ባሕር ዳር የገቡ  ሕጻናትን  አግኝቶ  ለምን  አንደመጡ  በጠየቃቸው ጊዜም ፤ ከቤተሰብ  አለመስማማት፣  የወላጅ ሞት እና ሌሎች ምክንያቶች ለጎዳና ሕይወት እንደዳረጋቸው ተናግረዋል።

በአማራ ክልል ሴቶች፣ ሕጻናት እና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ የሕጻናት መብት እና ደህንነት ጥበቃ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አሻግሬ ዘውዴ ለዶይቼ ቬለ DW እንደተናገሩት ደግሞ የጎዳና  ሕጻናት ተመልሰው  ወደ ከተማ  እንዳይገቡ እና ሌሎችንም እንዳይስቡ  የሚያስችል የተሀድሶ ማዕከል ለመገንባት ታቅዷል።  

በበጀት ዓመቱ ከ234ሺህ  በላይ  በችግር ላይ ያሉ ሕጻናትን እና ከ4600 በላይ የጎዳና ተዳዳሪ ሕጻናትን የመለየት እና የመመዝገብ ሥራ መከናወኑን አብራርተዋል። ለችግር ከተጋለጡት ሕጻናት መካከል 150ዎቹን በአገር ውስጥ አሳዳጊዎች መሰጠታቸውን፣ በርካቶቹ  ደግሞ የስፖንሰር ሺፕ አገልግሎት እንዲያገኙ መደረጉን ተናግረዋል።

ከተለዩ የጎዳና ተዳዳሪዎች መካከልም 270 ሕጻናት ወደየቤተሰቦቻቸው መቀላቀል መቻሉን አቶ አሻግሬ ተናግረዋል። የ ሕጻናቱን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ከንግዱ ማኅበረሰብ፣ ከባለሀብቱ፣ ከመንግሥት ሠራተኛውና ከኅብረተሰቡ ከ75 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡንም አመልክተዋል።

እንደዚሁም  የ108 የመንግሥት ቢሮ ሠራተኞች  ከወር  ደመወዛቸው  እቆረጡ  520  ሕጻናት ያለምንም  ችግር የትምህርት ቤት  ወጪ ተሸፍኖላቸው እንዲማሩ  እየተደረገ  እንደሆነ  አቶ አሻግሬ ተናግረዋል።

ዓለምነው መኮንን

ሸዋዬ ለገሠ

ተስፋለም ወልደየስ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች