ለግሪክ መላ ፈላጊዉ የአዉሮጳዉ ጉባኤ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 12.02.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

ለግሪክ መላ ፈላጊዉ የአዉሮጳዉ ጉባኤ

የአዉሮጳዉ ኅብረት ቋሚ ፕሪዝደንት ሚስተር ኸርማን ቫን ሮምፖይ የጠሩት መደበኛ ያልሆነ ስብሰባ ትናንት በብራስልስ ተካሂዷል።

default

የአዉሮጳ መሪዎች በብራስልስ

በኅብረቱ የረጅም ግዜ የአኮኖሚ እቅድ እና በአሁኑ ወቅት በተለይ የዩሮ ተጠቃሚ የኅብረቱ አባል አገሮች ላይ በተጋረጠዉ የኢኮኖሚ ችግር በመወያየት የጋራ አቋም በመዉሰድ ተጠናቋል። ባለፈዉ ወር ስራቸዉን የጀመሩት ሮምፖይ የትናንትናዉን ስብሰባ በተለይ የጠሩት በአለም አቀፍ ደረጃ የደረሰዉን የፊናንስ ቀዉስ ለመቋቋም እና በተለይ በግሪክ በደረሰዉ ችግር ዙርያ ለመወያየት ነበር።

ገበያዉ ንጉሴ/አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሠ